Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ሽፋንና አጠቃቀም ዙሪያ ለሚያደርገዉ ጥናትና ምርምር ስራ ዝግጅት ለመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ሰጠ።

ለኢንስቲትዩቱ በህግ ከተሰጡት ተግባራት መካከል በክልሉ የሚስተዋሉ ዋና ጤና ችግሮች ዙሪያ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ በግኝቶቹ መነሻ የመፍተሄ ሀሳቦችን መጠቆም ይገኝበታል። በዚሁ መሰረት በያዝነዉ አመት በተለያዩ ጤና ችግሮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ከምርምር ስራዎቹ መካከል አንዱና ልዩ ትኩረት የተሰጠዉ በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ተደራሽነትና ከአጠቃቀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ የሚካሄደዉ ጥናትና ምርምር ስራ ሲሆን ምርምሩ ሲጠናቀቅ ግኝቱ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል የጎላ ሚና እንደሚኖረዉ ይገመታል።

የስልጠና መድረኩን ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዪት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ እንደገለፁት የሕ/ሰባችንን ጤና ለማሻሻል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሳይንሳዊ ጥናይና ምርምር መደገፊ እንዳለባቸዉ ገልፀዉ ይህንን ለማድረግ የሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል። አክለዉም የጥናትና ምርምር ስራዉን ዉጤታማ ለማድረግ የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣሪዎች ሚና የጎላ በመሆኑ በልዩ ትኩረትና ጥንቃቄ እንዲሰራ አሳስበዋል።

በስልጠና መድረኩ ላይ ከክልሉ ጤና ቢሮ ፣ከሕብረተሰብ ጤና ኢንሰ‍እቲትዩና ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተመራማርዎች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸወ‍ኡ አካላት ተገኝተዋል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሀዋሳ/ሲዳማ

ሚያዝያ 1/2016 ዓ፡ም

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *