Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ለድንገተኛ ክስተቶች ዝግጁ የሆኑ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማት ለመፍጠር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ‘Resolve to save life Ethiopia’ ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በክልሉ ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ ክስተቶችን በአግባቡ በመቃኘት፣በጊዜ በማሳወቅና ምላሽ በመስጠት የህ/ሰባችን ጤና ለማሻሻል በጤና ተቋማት ሊከሰቱ የሚችሉ ብክለቶችን ለመቀነስ ስልጠና ተሰቷል።

በዕለቱ  ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምትክል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ ሲሆኑ በክልላችን ድንገተኛ  ክስተቶችን ቀድሞ በመከላከልና ስከሰቱ ፈጣን ምላሽ በመስጠት በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም ስልጣኞች ከዚህ ስልጠና በቅ ዕውቀት አግኝቶ በቀጣይ የሚጠበቅባቸው ተግባራትን በብቃት እንዲወጡ አሳስቧል።

በመድረኩ ከ Resolve to save life Ethiopia ፣ከወረዳ በሽታ መከላከል አስተባባሪዎችና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ባለሙያች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት ተሳትፈዋል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሚያዚያ 07/2016 ዓ.ም

ሀዋሳ,ሲዳማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *