Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

ከትግራይ ክልል ጤና ምርምር እንስቲትዩት ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተወጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የስራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ።

የልምድ ልውውጥ ቡድን አባላትን እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት መግቢያ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሲሆኑ በክልሉ እየተተገበረ ያለውን የመረጃ አያያዝ /ዳታ ማናጅመንት ሲስተም ፣ ነፃ የስልክ ጥሪ ማእከል (free call center) ፣ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፣ የክልሉ ላቦርቶሪ እና ጤና ምርምርና ተክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ላይ ገለጻ እና ምልከታ በማድረግ ልምድ ልውውጥ አድርጓል።

በትግራይ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና መሬጃ ቅመራ እና ትንተና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሴምሀል ሀጎስ በበኩላቸው በክልሉ ለተደረገው መልካም አቀባበል አመስግነው በልምድ ልውውጥ በርካታ ልምድ እንደቀሰሙ ገልፀዋል።

በክልላችን በሶስት ወር ውስጥ እደዚህ አይነት ልምድ ልውውጥ ሲካሄድ የዛሬው 4ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በፊት የጋምቤላ፣ የአፋር ክልል እና አዲስ አበባ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ ማካሄዳቸው ይታወሳል። ይህ የሚያሳው ኢንስቲትዩታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን ያሳያል።

በመጨረሻም፥ ዶ/ር ደመነ እንደገለጹት በቀጣይነት ተቋማችን የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence) ለማድረግ ተግተን እንሰራለን ብለዋል።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት

ሲዳማ/ሀዋሳ

14/08/2016 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *