የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የ4 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና የወባ ማሕበራት በተገኙበት አካሄደ፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ በመድረኩ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዘርፈ-ብዙ ተግባራት እንደተተገበሩ ገልፀው የወባ ጫናን ለመቀነስና ለመከላከል ከአካባቢ ቁጥጥር ስራ ባለፈ ሕብረተሰቡ የፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭትንና የአልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም እንዳለበት ገልፀዋል። በመቀጠልም የሪፖርት ሙሉዕነትንና ወቅታዊነት በመጠበቅ ፣ የግምገማ እና ግብረ መልስ ስርዓትን በመዘርጋት እና ተቋማዊ አንድነትን ማጠናከርን ባህል…
Read more