ሳምንታዊ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ክስተት አስተዳደር ስርዓት (Regional Incident Management System) በክልሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (PHEOC) ሥራዎች በዛሬዉ ዕለት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ፣ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በክልሉ አንዳንድ አከባቢ የተከሰቱ የኮሌራ ወረርሽኝ እና የወባ በሽታ ስርጭት ያለበት ደረጃ ተገምግሟል፡፡ መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ ከክረምት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰቱ የኮሌራ ወረርሽኝ እና የወባ በሽታ ስርጭት ከሚጠበቀዉ በላይ መሆኑ አሳሳቢ የህብረተሰብ ጤና…
Read more