Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

News

ሲ/ብ/ክ/መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ለሁለት አቅመ ደካማ ቤተሰብ ያስገነባውን ቤት አስረከ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን ሲያስገነባ የቆየዉን ቤት በማጠናቀቅ አስረከበ። በቤት ርክክብ መርሀግብር ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ስናገሩ እነኝህ ቤተሰቦች ቀደም ስል እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ፀሀይና ዝናብ እየተፈራረቀባቸዉ ከልጆቻቸዉ ጋር እየኖሩ መቆየታቸዉን ጠቅሰዉ በኢንስቲትዩቱ አመራርና ሰራተኞች በተደረገላቸዉ…
Read more

በጤና ሚኒስቴር መሪነት በዛሬው ዕለት የአለም አቀፍ የጤና አጋሮችና ሌጋሲ ድርጅቶች በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ የተሰሩ ስራዎችን ለመጎብኘት ወደ ክልሉ ገብተዋል።

እንግዶቹ ወደ ሀዋሳ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና ማኔጅመንቱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከተለያዩ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የተወጣጡ ልዑካን ቡድኖች በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ ጤና ተቋማት የሚሰጡ ጤና አገልግሎቶችን ተዘዋውረው እንደሚጎበኙ ለዚሁ የወጣው መርሃ ግብር ያሳያል። የክልሉ ጤና ቢሮጥር 20/2017 ዓ.ም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል (South West Ethiopia) ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል በአቶ ታምራት ቦጋሌ የሚመራ ቡድን ከሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለመጡ ልዑካን ቡድን አባላትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ በአጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በመቀጠልም እንግዶቹ በተቋሙ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች አማካኝነት የሥራ ምልከታና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል። በተጨማሪም የልዑካን ቡድን አባላት በርካታ ምርጥ ሥራዎች እንደተሰሩ በአስተያየታቸው ገልጸዋል። በክልላችን…
Read more

Resolve to Save Lives የሚባል መንግሰታዊ ያልሆነ ድርጅት በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ስር ለሚገኙ 23 ጤና ጣቢያዎች ከ4.6 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቆሻሻ ማሰባሰቢያ ባልዶችን፣ የወለል ማጽጃ ዕቃዎችን ፤ የለይቶ ማከሚያ አልጋዎችን፣ የሙቀት መለክያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተላላፊ በሽታ መከላከያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።

በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የጤና ቢሮ ኃላፏ ዶ/ር ስላማዊት መንገሻ፣ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ እንዲሁም የRTSL ፕርንስፓል ማናጀር ወ/ሮ ምንትዋብ ገ/እግዚአብሔር ተገኝቷል። የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩትጥር 17,2017 ዓ ምሀዋሳ

እንኳን ደስ አለን!!!

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ በBiosafety and Biosecurity star 4 ፣ የሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ LQMS -SLMTA star 4 እንድሁም የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ CSH ላቦራቶሪ በ Biosafety and Biosecurity star 3 በመድረስ ከሀገሪቷ ካሉ ላቦራቶሪዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና United kingdom Health Security ( UKHS) የዕውቅና Certificate ተበርክቶልናል።የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና…
Read more

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የብልፅግና ፓርቲ አባላት “ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ ቃል 2ኛ ዙር የአባላት ኮንፍረንስ ዛሬ መካሄድ ጀመረ።

በኮንፍረንሱ ላይ የብልጽግና ፓርቲን የእስካሁን ስኬቶች እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚያመላክቱ የተለያዩ ሰነዶች ለውይይት እየቀረቡ ይገኛል።የአመራር ግምገማ ሪፖርት እና የመ/ድርጅትና የህዋስ አመራር ሂስ ግለህስ ግምገማ የሚኖር ሲሆን በቀጣይም የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ ይካሄዳል። ሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩትጥር 7/2017ዓ.ምሀዋሳ

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በይርጋዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የተገነባውን የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካመርቀው ከፈቱ።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮጥር 04/2017 ዓ.ም በይርጋዓለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ የተገነባውን የኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ መርቀው ስራ አስጀምረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት የኦክሲጂን ማምረቻ ፋብሪካው ግንባታ መንግሥት ለጤና አገልግሎት መሻሻል የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያሳይ ገልፀዉ፥ ይህም የጤና አገልግሎት ጥራትን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው እንደገለፁት የኦክስጂን ማምረቻ ፋብሪካው የኦክስጅን…
Read more

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጤና ተቋማትን ጎበኙ !

ከትላንት ጀምሮ የተለያዩ አጀንዳዎችን ሲመሩ የቆዩት ክብርት የጤና ሚኒስትሯ በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ጤና ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ጎብኝተዋል። በዚህ ጉብኝት በክብርት ሚኒስትሯ የተጎበኙ ጤና ተቋማት መካከል የሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ፣ አዳሬ አ/ሆስፒታል ፣ ሞቲቴ ፉራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና የሚሊኒየም ጤና አ/ጣቢያ ይጠቀሳሉ ። በታዩት ጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶች ፥ የበሽታ መከላከል…
Read more

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተለያዩ መንግስታዊ ስራ ጉዳዮች ወደ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው !

በዛሬው ዕለት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ለተለያዩ መንግስታዊ ስራ ጉዳዮች ወደ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲደርሱ በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ እና በቢሮው ማኔጅመንት በሀዋሳ አውሮፕላን ጣቢያ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸዋል :: የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ክብርት ሚኒስትሯን እንኳን ደህና መጡ በማለት አቀባበል ካደረጉ በኋላ በክልሉ መልካም የቆይታ…
Read more