Skip to content መስከረም11/2017ዓ.ም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ መድረኩን በንግግር በከፈተበት ወቅት እንደተናገሩት ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመለየት፣ ለማከምና ለመቆጣጠር የላቦራቶሪ አገልግሎት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልፀዋል።
አክለውም ም/ዋና ዳይሬክተር ህክምና አገልግሎቱን ለማሻሻል የላቦራቶሪ አገልግሎቱ እየዘመነ እንደሆነ የገለፁት ም/ዋና ዳይሬክተሩ እንደ ክልል የጤና ተቋማትን ላቦራቶሪ ጥራት ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራ እየሰራ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው ተቋማት እርስ በርስ ተባብረውና ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አሳስቧል።
በሌላ በኩል የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ ማዕረግ የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ ተገኝተው መልዕክት ያስተላልፉ ሲሆን የህክምና አገልግሎት የላቦራቶሪ አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ SBFR፣ደህንነት(saftey) እና SLIPTA ዋና ዋና ትኩረት የተደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰው የሆስፒታል ሀላፊዎች በጥብቅ እንድከታተሉ አሳስቧል።
አክለውም በጥራት ቁጥጥር እና በጂንኤክስፐርት አጠቃቀም ላይ ጥሩ አፈጻጸም ላበረከቱ ሆስፒታሎች የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
በመጨረሻም የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ አዳቶ አዴላ በ2017 በጀት ዓመት 8 ተቋማትን ጨምረው በዚህ ስርዓት እንደምከታተሉ በመግለጽ ተቋማትም የራሳቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልጿል።
በመድረኩ የተገኙት የሆስፒታል ስራ አስኪያጆች፤ የላቦራቶሪ ሀላፊዎች የዞን ጤና ተወካዮች እና የኢንስቲትዩት ማኔጅመንት አባላት ናቸው ።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
መስከረም 11/2017 ዓ.ም
- by admin
- on September 30, 2024
0