የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለዞኖች፣ ለወረዳዎችና ለጤና ተቋማት የኮምፒውተር ድጋፍ አደረገ።
የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ግንቦት 12/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ከ 12,283, 000 ብር በላይ ተገዝቶ የተበረከተለትን 111 ኮምፒዩተር ዴስክ ቶፕ በክልሉ ለሚገኙ ለሁሉም ዞኖች፣ ወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች እና ሆስፒታሎች እንዲሁም ከፍተኛ ቁጥር ተገልጋዮችን ለሚያገለግሉ ጤና ጣቢያዎች የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር መረጃ አስተዳደርን ለማዘመን / PHEM &IDSR Digitalization/ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል ።
በርክክቡ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በመልዕክታቸው ፦ድጋፉ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር መረጃዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ ዘላቂ እና ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት ለመገንባት ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል ።
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ የተረከቡትን ኮምፒውተሮች ለታለመላቸው ዓላማ እና የሥራ ክፍል ብቻ በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስበው፣ ጤናማ ማኅበረሰብ ለመገንባት በመረጃ የተደገፈ የጤና ሥርዓት መገንባት የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር እንደሚጠይቅ ጠቁመዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የዞን ጤና ዴስኮች፣ የወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች ፣ የሆስፒታል ኃላፊዎች፦ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር መረጃዎችን በአንድ ሥርዓት ሥር በማደራጀትና በመተንተን የተሻለ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት ለመፍጠር እንደሚያስችል ተናግረው፥ የተደረገላቸውን ድጋፍ አድንቀው ለኢንስቲትዩቱ ምስጋና አቅርበዋል ።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 12 /2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት:
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
See less







