የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ሽፋንና አጠቃቀም ዙሪያ ለሚያደርገዉ ጥናትና ምርምር ስራ ዝግጅት ለመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ሰጠ።
ለኢንስቲትዩቱ በህግ ከተሰጡት ተግባራት መካከል በክልሉ የሚስተዋሉ ዋና ጤና ችግሮች ዙሪያ ሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮችን በማካሄድ በግኝቶቹ መነሻ የመፍተሄ ሀሳቦችን መጠቆም ይገኝበታል። በዚሁ መሰረት በያዝነዉ አመት በተለያዩ ጤና ችግሮች ዙሪያ ልዩ ልዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ በማካሄድ ላይ ይገኛል። ከምርምር ስራዎቹ መካከል አንዱና ልዩ ትኩረት የተሰጠዉ በክልሉ የመጸዳጃ ቤት ተደራሽነትና ከአጠቃቀም ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ…










