7794
ከክፍያ ነጻ የስልክ መስመር በመጠቀም ድንገተኛ አደጋዎች ሲያጋጥመዎ ጥቆማ ይስጡ !! በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት የካትት 24/2016 ዓ.ም ሲዳማ/ሀዋሳ
Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.


ጤናማ ፣ አምራችና የበለጸገ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንቅፋት የሚሆኑ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች እና የተከሰተው የኩፉኝ ወረርሽኝ ስለመተላለፊያ መንገዶችና የመከላከያ ስልቶችን አስመልክቶ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ማስጨበጥ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው ፤ ለተሳታፊዎች የተከሰተው ወረርሽኝ ለመከላከል በተቀናጀ መልኩ ሊመራ እንደሚገባ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ አሳሰቡ። በመጨረሻም ከሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው ለተነሱ…

28ተኛዉ አገር አቀፍ የጊኒዎርም በሽታ ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የካርተር ሴንትር፣ የአለም ጤና ድርጅት እና የክልሎች ጤና ቢሮ እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው የምክክር መድረክ ላይ በዓመቱ ዉስጥ የተከናወኑ በርካታ ሥራዎች አፈጻጸም የሚቀርብበት፣ የሚገመገምበት እንዲሁም ዉይይት የሚካሄድበት እና…

በኢንስቲትዩቱ የባክቴሪያል፣ የፓራሳይቲክ እና እንሰሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ እና ዶ/ር መሳይ ኃይሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም ም/ዋና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ዓመታዊ የጸረ-ተህዋስያን መድሃኒቶች ብግርነት Ani-microbial Resistance (AMR) የዳሰሳ ጥናት የምክክር መድረክ የካቲት 18 እና 19/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የምክክር መድረኩ ዋና ዓለማ ኢ.ኤ.አ…

የክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ ሽኝት እና የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት የክልል ጤና ቢሮ የስራ ኃላፊዎች የተጠሪ ተቋማት፣ የጤና ሚኒስቴር እንደዚሁም የፌድራል እና በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ስር የሚገኙ የሆስፒታሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በደማቅ ሁኔታ አከናውነዋል፡፡ በመድረኩ ሽኝት የተደረገላቸው ክብርት ዶ/ር ሊያ በጤና ሚኒስትርነት ሃገራቸውን በማገልገል ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጾ እና በጤናው ዘርፍ መሪነት ላስመዘገቧቸው…

————————— ክቡር ዶ/ር አየለ ተሾመ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስብሰባ አዳራሽ በመገኘት በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ይህ ለጤናው ሴክተር ትልቅ እገዛ ሊያደርግ የሚችለው ፕሮግራም መጀመርና የክፍሉ መቋቋም በሀገር አቀፍ ደረጃ የማሕበረሰብ ጤና እርምጃዎች መረጃን ለማመንጨት እና ለመተንተን ብሎም ለመተርጎም፣ ለመጠቀም እና ለማጋራት እንደሚያስችል አስረድተዋል። ክቡር የጤና ሚኒስትር ዴኤታው አያይዘውም…

ዛሬ የካቲት 10/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ከሥራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በመቀናጀት በክልሉ ስር ከሚገኙ ከተለያዮ ወረዳዎች የተወጣጡ የጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ከአራቱም ዞን የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊዎችና የጤና ክፍል ሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቀን የካቲት 10/2016 ዓ.ም በክልሉ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ ወረርሽኝ ያለበት ደረጃ ገምግሞ ደካማ ጎኑን…

በመድረኩ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና ከአራቱም ዞኖች የጤና ዘርፍ ዳይሬክተሮች እና ጉዳዩ የሚመለክታቸው አካላት ተሳትፈዋል። የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ለእቅዱ ስኬታማነት ሁሉም ትኩረት ሰጥተው በመሥራቱ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረው በቀጣይነትም በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፍትም ሆነ ከተከሰቱ በኃላ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት፤ የምርምር ሥራዎችን ማጠናከር እና የላቦራቶሪ ሥራዎች አቅም በማሳደግ ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ…

ዛሬ 28/05/2016 ዓ.ም በሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና ትንተና ዳይሮክቶሬት በሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጤና መረጃ ዘመቻና ትግበራ ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት (Data campaign and implementation workshop) ተካሂዷል::የዕለቱን መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ ናቸው፡፡ የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራና…

ታህሳስ 26/2016 ዓ.ም ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ሀዋሳ የዕለቱን እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሲሆን በመልዕክታቸው፣ እንዳነሱት ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ አራት ዋና ዋና ሥራዎችን ማለትም ድንገተኛ የጤና አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ፣ ደረጃውን የጠበቀ የላብራቶሪ አግልግሎት ለሁሉም ጤና ተቋማት ማዳረስ ፣ጥራት ያለውን መረጃ በአንድ…