ስለ ማርበርግ በሽታ ይወቁ እራስውን ይጠብቁ!

Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.



ከዚህ በፊት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና ከ”National Information Platform Nutrition (NIPN)” ፕሮጀክት ጋር በትብብር ለመስራት የጋራ ስምምነት መፈራረማቸውና በክልል ደረጃ ይህ ፕሮግራም መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ይህንን ለማጠናከርና የተለያየ ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ ለመውሰድ ከዛምቢያ፤ ከኒጀር እና እና ከኢትዮጵያ የፕሮጀክቱ ኃላፊዎች በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመገኘት ሰፊ ውይይትና ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ በውይይቱ በሲዳማ ክልል ሕብረተስብ…

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ እና ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች በተገኙበት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር ማዕከል በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተካሄደ ያለው የሰራ እንቅስቃሴ እና መሰረታዊ የዲጂታላይዜሽን ስልታዊ እስትራቴጂ ተግባራዊነት ውጤታማ መሆኑን የካቲት 17/2018 ዓ.ም ይፋ አደረገ፡፡ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር የፕሮግራሙን መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደገለጹት ይህ የልሕቀት ማዕከል…

ሀዋሳ፤ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ”ኢትዮጽያ ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ቃል የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የብልፅግና ህብረት በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል ። የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሀዊ እንዲሁም የተጀመሩ ሥራዎችን ዉጤታማነት ለማስቀጥል የፖርቲዉ አባላት ቁርጠኛ መሆን…

ስልጠናውን ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ከእርዳታ ተላቀን ወደ ተሻለ የእድገት ደረጃ ለመድረስ ቁርጠኛ የሆነ አመራርን አስፈላጊነት አጽኖት ሰጥተዋል፡፡ በጤናው ዘርፍም ቢሆን ነገን ለመቀየር ብቃት ያለው አመራር ለመፍጠር የፕሮግራሙን አስፈላጊነት ገልጸዋል፡፡ ፕሮግራሙ በተለይ ለሴቶች ትኩረት በመስጠት በዚህኛው ዙር አብላጫውን ድርሻ እንዲይዙ መደረጉን የተናገሩት ዶ/ር መቅደስ፤ ተመራቂዎች ግንባር ቀደም…

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የውጫዊ ጥራት ቁጥጥር ማዕከል ከሆኑ ተቋማት ላቦራቶሪ ባለሙያዎች እንዲሁም ከየወረዳ ለተወጣጡ ለቲቢና ወባ ተወካዮች ”የውጫዊ ጥራትና ቁጥጥር መተግበሪያ ዳታቤዝ” በሚል ርዕስ ለአምስት ቀን ስሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ። በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በአጠቃላይ ውይይት እንደገለጹት የተቀናጀ ውጫዊ ጥራት ቁጥጥር በወባና በቲቢ ላይ እየተሰራ የቆየ ብሆንም እንደ ሀገር ከእስላይድ መሰብሰብ አንስቶ…

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዳር 30/2018 ዓ/ም የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለሀይማኖት ተቋማት በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል። የኢንስቲትዩቱ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በድሉ ባዴጎ ባስተላለፋት መልዕክት የማርበርግ ቫይረስ በሀገራችን መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ወረርሽኙን አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። አቶ በድሉ አክለውም ስራውን…