እንኳን ደስ አለን!!!

።።።።።።።።።።።።።።።

ጤና ሚኒሰቴር ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን አሳወቀ ።

የጤና ሚኒስቴር ሀገራችን ኢትዮጵያ ከማርበርግ በሽታ ወረርሽኝ ሙሉ በሙሉ ነጻ መሆኗን በገለጸበት መድረክ ላይ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ስለአከናወነው ተግባራትና ስላበረከተው አሰተዋጽኦ ከህዝብ ተወካይ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ከተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ እጅ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ዋንጫና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተቀብለዋል ።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ለተገኘው አስደናቂ ስኬትና እውቅና የተሰማውን ደስታ እየገለጸ በ MVD ወረርሽኝ ምላሽ ሥራዎች ላይ የተሳተፋችሁት አካላት በሙሉ አንኳን ደስ አላችሁ !!!

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጥር 18/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://sphi.gov.et/

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *