Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

በክልላችን ከፍ እያለ የመጣውን የወባ ወረርሽኝ ለማስቆም ዘርፈ ብዙ ስራ እየተሰራ ይገኛል፤ ከእነዚህም ስራዎች አንዱ የሆነው የምርመራውን አቅምና ጥራት ማሻሻል ነው የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ከክልል ጤና ቢሮ እና ከይርጋለም ህክምና ኮሌጅ ጋር በመተባበር ”መሠረታዊ የወባ ምርመራ በማይክሮስፒ” በሚል ሪዕስ ከህዳር 9-13/2017ዓ/ም ለላቦራቶሪ ሰራተኞች ስሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያው ላይ የተገኙት የኢንስቲትዩቱ ም/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ በክልላችን ያለውን የወባ ወረርሽኝ ለመግታት የላቦራቶሪ ባለሙያዎች ሚና ትልቅ መሆኑን ገልጸው የነበሩትን ክፍተቶች ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነም በመግለጽ በዚህ ስልጠና ያካበቱትን እውቀት በተግባር እንዲያሳዩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በበኩላቸው በየተቋማቱ ያሉ የላቦራቶሪ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት ዘርፈ ብዙ ስራ እየተሰራ እንደሆነ ገልጸው በተለይ ወባን በማይክሮስኮፒ በመመርመር ላይ ጥራቱን ለማስጠበቅ የጀመርነውን ስራ እናስቀጥላለን ብሏል።

በመጨረሻም ከይርጋለም ሆስፒታል ህክምና ኮሌጅ(CPD Center) ጋር በመተባበር ለሠለጠኑ ባለሙያዎች ሰርተፍኬት በማበርከት ስልጠናው ተጠናቋል።

የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት

ህዳር 13/2017ዓ/ም

ሀዋሳ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *