የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመድኃኒት የተላመዱ ተዋህስያን መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የምክክር መድረክ ማካሄዱ ተገለጸ
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 11/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በመድኃኒት የተላመዱ ተዋህስያን መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የምክክር መድረክ ማካሄዱን አስታውቋል ።
በመድረኩ ላይ ጸረ ተዋህስያን መድሃኒቶችን በትክክል መጠቀም፣ መድሃኒቶችን የተላመዱ ተዋህስያንን በፍጥነት መለየት እና ተገቢ ህክምና መስጠት ላይ አጽንዖት ተሰጥቷል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ በሆስፒታሎች የማይክሮባዮሎጂ ላቦራቶሪ አቅምን ማጠናከር እና ማስፋፋት ወቅታዊ አስፈላጊነት እንዳለው ገልጸው፣ በዚህ ረገድ የአቅም ግንባታ ስራዎች በእቅድ ተይዘው እየተከናወኑ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
መድረኩ መድሃኒቶችን የተላመዱ ተዋህስያንን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ስራ እና የተቋማት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አመላክቷል ።
በውይይት ወቅት ተሳታፊዎች አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት መድሃኒቶችን ያለ ሐኪም ምክር መጠቀም፣ አላስፈላጊ የፀረ-ተዋህስያን አጠቃቀም ችግሩን እያባባሰ መሆኑን ጠቅሰው፣ ህብረተሰቡን በማስተማር እና የጤና ተቋማት ቁጥጥርን በማጠናከር ችግሩን መቀነስ በትብብር መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም የኢንስቲትዩቱን ላቦራቶሪ በመጎብኘት የሚሰጡ አገልግሎቶችንና የተገነባውን የላቦራቶሪ አቅም ተመልክተዋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ግንቦት 11/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት:
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
See less






