የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት አፈጻጸምን ገምግሞ የ2019 ዓ.ም ትኩረቶችን አስተዋወቀ።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ፣ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ የጤና ተቋማት የዕውቅናና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።
በመድረኩ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ እንደገለጹት፣ 2018 በጀት ዓመት ለኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ስኬቶች የተመዘገቡበት ዓመት ሲሆን፣ ይህም ውጤት በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቅንጅትና በተቀናጀ አሠራር በመሥራታቸው የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል። ለስኬቱ አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉም አካላትም ምስጋና አቅርበዋል።
ዶ/ር ዳመነ አክለውም፣ በ2018 በጀት ዓመት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋትና የታዩ ክፍተቶችን በማረም፣ በ2019 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ ሁሉም አመራሮችና ፈጻሚዎች በተዘጋጀ መንፈስ እንዲሠሩ አሳስበዋል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ አቅርበዋል።
በሪፖርታቸውም በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን፣ የተለዩ ክፍተቶችን እና በ2019 በጀት ዓመት በትኩረት የሚከናወኑ የላቦራቶሪ ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
አቶ አዳቶ እንደገለጹት፣ ጥራት ያለውንና ተደራሽ የላቦራቶሪ አገልግሎት ማረጋገጥ፣ የጤና ዘርፉን የልማት ማነቆዎች የሚፈቱ ተግባራዊ ምርምሮችን ማካሄድ፣ እንዲሁም ከጤና ተቋማትና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ያለውን ቅንጅት ማጠናከር በ2019 በጀት ዓመት ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል።
በተጨማሪም በሲዳማ ክልል የሚሰጡ የላቦራቶሪ አገልግሎቶች ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃዎችን እንዲያሟሉና የተሻለ የጤና ሥርዓት እንዲገነባ ኢንስቲትዩቱ በትኩረት እየሠራ መሆኑ ተገልጿል።
እንደተገለጸውም፣ በቀደመው የማርበርግ ወረርሽኝ ስጋት ወቅት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ80 በመቶ በላይ የላቦራቶሪ ድጋፍ በመስጠት ጉልህ አስተዋፅኦ ማበርከቱ ተጠቅሷል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የጤና ጣቢያዎች፣ የመጀመሪያ ደረጃ፣ አጠቃላይና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሎች በተቋም ደረጃ የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 23/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less


































