የሲዳማ ክልል የምክር ቤት የልዑካን ቡድን የሁለተኛ ቀን ጉብኝት በይርጋለም ከተማ ጤና ጣቢያ ተጠናክሮ ቀጠለ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም
በሲዳማ ክልል የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎችና አመራሮችን ያካተተው የልዑካን ቡድን የሁለተኛ ቀን የመስክ ጉብኝቱን በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ይርጋለም ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጣቢያ በማካሄድ፣ በጤና ዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ ተጨባጭ ለውጦችንና የአገልግሎት ጥራትን በተግባር ተመልክቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የጤና አገልግሎት ጥራት፣ የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ የቤተሰብ ጤና ቡድን (FHT) አፈፃፀም፣ የፅዱ ጤና ተቋማት ትግበራ እና የጤና ዘርፉ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳ አፈፃፀም በዝርዝር ተቃኝቷል።
የይርጋለም ከተማ ጤና ጣቢያ አመራሮች በ2015 እስከ 2018 ዓ.ም በተቋሙ የተመዘገቡ ዋና ዋና ለውጦችን፣ የቤተሰብ ጤና ቡድን አፈፃፀምንና የፅዱ ጤና ተቋማት ፕሮግራም እንቅስቃሴን ለልዑካኑ በሰፊው አብራርተዋል።
በጤና ጣቢያው የሚሰጡ መሠረታዊ የጤና አገልግሎቶች ፍትሃዊ፣ ተደራሽና ጥራት ያላቸው መሆናቸው በጉብኝቱ ተመልክቷል። በተለይም የእናቶችና የሕፃናት ሞትን ለመቀነስ፣ ተላላፊ በሽታዎችን በማህበረሰብ ደረጃ ለመከላከልና የጤና ማስተዋወቅ ሥራዎችን ለማጠናከር የሚከናወኑ ተግባራት ቀርበው ተገምግመዋል።
ተቋሙ የጤና መረጃ ሥርዓቱን በማጠናከር፣ EMR እና Dagu Systemን በሥራ ላይ በማዋል የታካሚ መረጃና የመድኃኒት አስተዳደርን በዲጂታል መንገድ እያዘመነ መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም የሕክምና ግብዓቶች፣ መድኃኒቶችና ዘመናዊ የምርመራ መሣሪያዎች አቅርቦት መሻሻሉ ተጠቁሟል።
ጤና ጣቢያው የእናቶችና ሕፃናት ጤና፣ ክትባት፣ OPD፣ ላቦራቶሪ፣ ፋርማሲ፣ ቲቢና HIV አገልግሎቶችን በተሟላ ሁኔታ እየሰጠ ሲሆን፣ ለወጣቶች ምቹ ክሊኒክ፣ የዓይን ሕክምና፣ የECD እና የአልጋ ሕክምና አገልግሎቶች ተቋሙን ከሌሎች ጤና ጣቢያዎች የሚለዩ ጠንካራ ተግባራት መሆናቸው ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ የእናቶች ማቆያን፣ የቤተሰብ ጤና ቡድን አሠራርን እና የፅዱ ጤና ተቋማት ትግበራን ፣ የመድኃኒት አያያዝ ፣ የድንገተኛ ክፍሎችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮች የነበሩ ጉዳዮች የተፈቱበትን በተግባር ጎብኝቶ አድናቆቱን ገልጿል። በዚሁ ወቅት የጤና ዘርፉ የ2030 ዓ.ም ግቦችን ለማሳካት የንፅህና አጠባበቅና የተላላፊ በሽታዎች መከላከል ቅድሚያ ሊሰጣቸው ከሚገቡ ተግባራት መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል።
ፅዱ፣ ምቹና ውብ የጤና ተቋማትን በመፍጠር በሽታን፣ አካል ጉዳትንና ሞትን ለመቀነስ የሁሉም አካላት ቁርጠኛ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል።
በማጠቃለያው የልዑካን ቡድኑ በጤና ጣቢያው የተመዘገቡትን አበረታች ውጤቶች በማድነቅ፣ የተጀመሩት የጤና ዘርፍ ለውጦች በቀጣይነት ተጠናክረው እንዲቀጥሉና ተደራሽነታቸው በመላው ክልሉ እንዲሰፋ አስፈላጊ መሆኑን አሳስቧል።
የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:




Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
YouTube:
Tik Tok:
See less






