በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በቀጣይ በሚተገበሩ ሀገራዊና ክልላዊ ዕቅድ፣ በፓርቲው ማንፌስቶ እንዲሁም በምርጫ መመሪያ ላይ የኢንስቲትዩቱ የብልጽግና ፓርቲ አባላት ዉይይት አደረጉ።
ሀዋሳ፤ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
”ኢትዮጽያ ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ ቃል የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የብልፅግና ህብረት በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሯል ።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሀዊ እንዲሁም የተጀመሩ ሥራዎችን ዉጤታማነት ለማስቀጥል የፖርቲዉ አባላት ቁርጠኛ መሆን እንዳለባቸዉ ተናግረዋል።
የብልፅግና ፖርቲ የሀገራችንን ህዝቦች ከተረጅነት ለማላቀቅ በመደመር መንገድ በመጓዝ ከተስፋ ብርሃን ወደ ሚጨበጥ ብርሀን ማሸጋገሩን ከዶ/ር ዳመነ ገለጻ ለመረዳት ችለናል።
የፓርቲ አባላት የሚገጥም ችግሮችን ወደ ዕድል መቀየር እንዳለባቸዉ እንዲሁም 7ተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸዉን አስተዎፆኦ ማበርከት እንደሚገባቸዉ ከመድረኩ ተገልጿል ።
በቀረበዉ ሰነድ ላይ ሰፊ ዉይይት በማካሄድ ከአባላቱ ለተነሱ ጥያቄዎች የሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ዉይይቱ ተጠናቋል።
የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሚያዚያ 30/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት:
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: https://www.sphi.gov.et/
See less







