በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል የማርበርግ ቫይረሰ በሽታ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የክልሉ ድንገተኛ አደጋ ማስተባበሪያ ጣቢያ (Emergency Operation Center) ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ድረስ የተሰሩ ስራዎችን ገምግሟል።
የአፈጻጸም ግምገማው መድረክ ተሳታፊዎች ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ፣ ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት እና ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ አጋር ድርጅቶች ሲሆኑ ፧ በክልሉ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረሰ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየዕለቱ የተተገበሩ ተግባራት ሪፖርት በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዝርዝር ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ። በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ…










