የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም በጀት አመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል ።
በመድረኩ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና ከአራቱም ዞኖች የጤና ዘርፍ ዳይሬክተሮች እና ጉዳዩ የሚመለክታቸው አካላት ተሳትፈዋል። የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ለእቅዱ ስኬታማነት ሁሉም ትኩረት ሰጥተው በመሥራቱ አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረው በቀጣይነትም በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ከመከሰታቸው በፍትም ሆነ ከተከሰቱ በኃላ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት፤ የምርምር ሥራዎችን ማጠናከር እና የላቦራቶሪ ሥራዎች አቅም በማሳደግ ውጤታማ ሥራ መሥራት እንደሚያስፈልግ…










