ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ በሚል መሪ ቃል በዛሬ ቀን መጋብት 6/2016 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የመንግሥት ሰራተኞች 2ኛ ዙር መሰረታዊ የፓርቲ አባላት ኮንፎራንስ አካሂዷል፡፡
በኮንፎራንሱም የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ አሸናፍ ኤልያስ ተገኝተዋል ፡፡ ከቡር አቶ አሸናፍ ኤልያስ እንዳሉት “ጠንካራ አደረጃጀት ሲፈጠር ጠንካራ ፓርቲ ይፈጠራል፡፡ ጠንካራ ፓርቲ ሲፈጠር ጠንካራ መንግስት ይኖራል፡፡” ስለዚህ የፓርቲ ስራ ማጠናከር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡










