በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውሰጥ የሚገኙ ሰዎች ሰዉነትን ያዳረሰ ሸፍታ እና ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት በተጨማርም ሳል ወይም የንፍጥ መዝረብረብ ወይም የዓይን ህመም (መቅላት) ሲኖር የኩፍኝ በሸታ ሊሆን ሰለሚችል ፈጥነው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ያግኙ።
ለበለጠ መረጃ በነፃ የሰልክ መሰመር 7794 ይደውሉ!!
በሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት


Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.



በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ (Evidence-Informed Decision-Making – EIDM) ጉባኤ በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ እየተካሄደ ሲሆን የጤና ስርዓቶችን በዕውቀት፣ በማስረጃና በትብብር ማጠናከር የወቅቱ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተገለጸ። በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ፣ ጉባኤው የጤና ስርዓቶችን በዕውቀት፣ በማስረጃና በትብብር ለማጠናከር ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። ዶክተር መሳይ…

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በክረምት ወቅት ከፍተኛ ዝናብ ከመዝነብ ጋር ተያይዞ በተዳፋታማና ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የምትኖሩ የክልላችን ሕብረተሰብ በሙሉ ፤ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰት ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ና በተጨማሪም ስጋቱ ያለባቸው ወረዳዎች፤ የወረዳ ጤና ጽ/ቤቶችም ለሕብረተሰቡ የቅድመ-ማስጠንቀቂያ መልዕክት እንድታስተላልፉና ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነሐሴ 11/2017 ዓ/ም ሀዋሳ ተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና…

Ethiopia Launches the First Regional Action Plan for Health Security —————————— በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የክልላዊ የጤና ደህንነት የዕቅድ አቅም ግንባታ ማስጀመሪያ አውደ ጥናት በሲዳማ ክልል በይርጋለም ከተማ ከነሀሴ 26 – 28/2017 ዓ.ም ተካሄደ። ይህ የክልላዊ የጤና ደህንነት ዕቅድና ትግበራ በአቅም ግንባታ ሂደት ውስጥ የስርዓት አስተሳሰብን እንደሚያሳድግ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ዕቅዱ ከአለምአቀፍ እና ከሀገር አቀፍ ደረጃ የተሻሉ ተሞክሮዎችን…

—————— ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የክልል ላቦራቶሪዎችን የሚሰጡትን የላቦራቶሪ አገልግሎት ተደራሽ እና ጥራቱን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል ግምታቸው 158 ሚሊየን ብር የሚጠጉ የተለያዩ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ አደረገ። የድጋፉ ዋና ዓላማው የሕብረተሰብ የጤና ችግር የሆኑት ተህዋሲያን የመለየት አቅምን ማሳደግ፣ የመረጃ ቅብብሎሽን ማዘመን፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደራሽ ላልሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የሚያግዙ የትሪፕል ፓኬጆች…

EPHI, Africa-CDC Continue to Strengthen Partnership —————————- የአፍሪካ ሲዲሲ ኢስተርን ሪጂናል ኮርዲኔሽን ሴንተር (Africa CDC Eastern RCC) ሪጂናል ዳይሬክተር ዶ/ር ማዚያንጋ ሉሲ ማዛባ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም የስራ ጉብኝት አደረጉ። የጉብኝቱ ዓላማም ማዕከሉ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር ዘርፎችን በመለየት የጋራ ግቦችን ለማስቀመጥ እንደሆነ ሪጅናል ዳይሬክተሯ ገልፀዋል። የኢትዮጵያ…

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም በኮንፈረንሱ መድረክ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንካራ ሀገር ለመገንባትና የተጀመረውን ፈጣን ልማት ለማስቀጠልና ለማሳለጥ በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት የአባላት ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል። እንደ ክልል ኢንስቲትዩቱ የህዝቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየሰራ እንደሚገኝ…