የዓለም አቀፉ ጌትስ ፋውንዴሽን ልዑካን በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ሥራዎች ያለበትን ደረጃ ጎበኙ።
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 30፣ 2018 ዓ.ም.
ከዓለም አቀፉ ጌትስ ፋውንዴሽን የተውጣጡ ከፍተኛ ልዑካን በሲዳማ ክልል እየተተገበረ ያለውን የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ (Public Health Emergency Management-PHEM) ሥርዓት በመጎብኘት የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።
ልዑካኑን የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በቢሯቸው ተቀብለው ስለ ክልሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት፣ የተገኙ ውጤቶችና የወደፊት እቅዶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት ልዑካኑ የበሽታዎች ቅኝት ሥርዓት፣ የሪፖርት ፍሰት፣ የመረጃ ጥራት ማረጋገጥ፣ የመረጃ ዲጂታላይዜሽን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀም እና በመረጃ ላይ ተመስርቶ የሚሰጥ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓትን በዝርዝር ተመልክተዋል።
በተጨማሪም በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃዶችና በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚሰጡ የPHEM አገልግሎቶችን በጥልቀት ገምግመዋል።
ልዑካኑ በጉብኝቱ የተመለከቱት የሥራ አፈጻጸም እጅግ አስደናቂ መሆኑን ገልጸው፣ በክልሉ ለሚከሰቱ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች የሚሰጠው ፈጣንና ተገቢ ምላሽ ከሀገራዊና ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ይህም የክልሉ የጤና ሥርዓት አቅም እያደገ መሆኑን የሚያሳይ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም የPHEM መረጃዎችን በDHIS2 ሥርዓት በወቅቱ የማስገባት አፈጻጸም ከ95 በመቶ በላይ የሪፖርት ሙሉነትና ወቅታዊነት ማስመዝገቡ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው 80 በመቶ ዒላማ በእጅጉ የላቀ ውጤት መሆኑን በማድነቅ ክልሉ በዚህ ዘርፍ ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን አፈጻጸም ማሳየቱን ገልጸዋል።
ጉብኝቱ በሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ሥርዓት የተመዘገቡ ውጤቶችን በሀገር ብሎም በዓለም አቀፍ አጋሮች ዘንድ ለማስተዋወቅና የቀጣይ ትብብርን ለማጠናከር ጠቃሚ አጋጣሚ መሆኑ ተጠቁሟል።
በጉብኝቱ ማጠቃለያ ልዑካኑ የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪን በመጎብኘት በክልሉ እየተሰጡ ያሉ የላቦራቶሪ አገልግሎቶችን፣ የምርመራ አቅምንና የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቶችን የተመለከቱ ስሆን በቀጣይነት አብሮ እንደሚሰሩ ቃል በመግባት ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል።
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ሀምሌ 30/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less






























