በሲዳማ ክልል የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታት ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱ ተገለጸ፡፡

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሰኔ16/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልሉ የወባ በሽታ ስርጭትን ለመግታትና የላቦራቶሪ ምርመራ ጥራትን ለማሻሻል ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ እንደገለጹት፦ ስልጠናው ባለሙያዎች ጥራቱን የጠበቀና ትክክለኛ የላቦራቶሪ ምርመራ በማከናወን የህብረተሰቡን ጤና አገልግሎት እንዲያሻሽሉ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የወባ በሽታ ጫናን ለመቀነስና ለማጥፋት የተለያዩ የመከላከልና በበሽታ የተያዙትን የማከም ስልቶች እየተተገበሩ መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በአሁኑ ወቅትም የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በሥራ ቦታቸው በመተግበርና ለሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው በማካፈል በወባ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር ሥራ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ ቀርቧል።

በሽታውን አስቀድሞ ለመከላከልና ስርጭቱን ለመግታት የአቅም ግንባታና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በቀጣይነት እንደሚጠናከሩ ተገልጿል::

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሰኔ 16/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *