በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የጤና አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 10/2018 ዓ.ም
በጤናው ሴክተር ለሚተገበሩ የሪፎርም ሥራዎች እና የለውጥ ሂደቱን ለማፋጠን ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና፣ ሪፎርሙ በአሁኑ ወቅት በዝግጅት ምዕራፍ ላይ መሆኑን ታሳቢ በማድረግ፣ ለሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና ለቢሮው ተጠሪ ተቋማት ከተወጣጡ ሠራተኞች እየተሰጠ ነው።
ስልጠናውን በይፋ የከፈቱት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል፣ የሪፎርም ክትትል ኮሚቴ ሰብሳቢ እና የዘርፈ ብዙ ምላሽ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት መኮንን በመልዕክታቸው ፦የጤና አገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያ ሪፎርም የዛሬንና የወደፊቱን ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት ቀልጣፋ፣ ተጠያቂና ውጤታማ ተቋማትን ለመገንባት ያለመ ስትራቴጂያዊ የለውጥ አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ እመቤት እንዳስረዱት፣ ሪፎርም ቀጣይነት ያለው የለውጥ ሂደት በመሆኑ አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በማካተት ከወቅቱ ጋር የሚጣጣም ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት መፍጠርን እንደሚጠይቅ አውስተው፤በተለይም የተበታተኑ ሥራዎችን ወደ አንድ ማዕቀፍ በማምጣት ውጤት ተኮር አሠራርን ማስፈን የዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጨማሪም፣ ይህንን ግብ ለማሳካት ከተለመዱ አሠራሮች በመላቀቅ በአስተሳሰብና በአሠራር ለውጥ የተደገፈ ዘመናዊ የሪፎርም አተገባበር መከተል እንደሚገባ ገልጸዋል።
ተቋማትን ማዘመን፣ የአገልጋይነት አስተሳሰብን ማጠናከር እና የሕዝብን እርካታ ማሳደግ የሪፎርሙ ዋና ዋና ትኩረቶች መሆናቸውን በማስታወቅ፣ የለውጡ ስኬት የሁሉንም ሠራተኞች ንቁ ተሳትፎና ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ በአፅንዖት አሳስበዋል።
በቀረቡ ተከታታይ ሰነዶች ስልጠናው በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እየተደረጉ ባሉ የሲቪል ሰርቪስና የመንግሥት ሪፎርም አሰራሮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የመንግሥት አደረጃጀትና አስተዳደር ሥርዓትን ማሻሻል፣ የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓትን መገንባት፣ ብዝሃነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ እንዲሁም ነፃና ገለልተኛ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት መፍጠር የሚሉ ቁልፍ ጉዳዮችን በስፋት ዳስሷል።
በተጨማሪም ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ጥራት ያለው የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ማረጋገጥ፣ የመንግሥት አወቃቀርና አስተዳደር ሥርዓትን ማዘመን እና የሠራተኞችን ብቃት በመመዘን ውጤታማ የሰው ኃይል ሥርዓት መገንባት ላይ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በዚሁ ወቅት ሰነድ አቅራቢዎች እንደገለጹት፣ ተቋሙ መንግሥት ያስቀመጠውን የሪፎርም ትግበራ አቅጣጫ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር የሚያስችሉ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸው፣ የሪፎርሙ ስኬት የሁሉንም ሠራተኞች ንቁ ተሳትፎና ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ አሳስበዋል።
የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ
10/10/2018 ዓ.ም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
Website: https://www.shb.gov.et
Facebook:




Telegram : https://t.me/SidamaRHB
Twitter: https://x.com/sidama_health_bureau
WhatsApp:
YouTube:
Tik Tok:
See less






