የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ እያካሄደ ነው።

‎በመድረኩ ላይ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ፣ የሲዳማ ብ/ክ/መ ጤና ቢሮ ማኔጅመንት አባላት፣የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ም/ዋና ዳይረክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ፣ የEPSS ሀዋሳ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ዘመን ለገሰ ፣የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞችን ጨምሮ የዞኖች፣ የወረዳዎችና የጤና ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

‎በመድረኩ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ መልዕክት በማስተላለፍ ስብሰባውን በይፋ ከፍተዋል።

‎የዞን፣ የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያና የወረዳዎች ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ የሆስፒታልና የጤና ጣቢያዎች ሥራ አስኪያጆች፤ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት እና የኢንስቲትዩቱ ጠቅላላ ሠራተኞች በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።

‎የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጳጉሜ 4/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *