Skip to content የዛሬ አንድ አሜት ገደማ Resolve to Save lives የሚባል መንግስታዊ ያልሆኔ ድርጅት ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ እና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በ 8 ወረዳ እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ በ23 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ከተከሰቱ በብቃት ለመመከት እንዲሁም በዘላቅነት መደበኛ የጤና አገልግሎቶች ሳይስተጎጉል ለማስቀጠል ዝግጁ የሆኔ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ አሃድ የመፍጠር ፕርግራም የመጀመሪያ ዙር የPHEM and IPC mentorshop የመጀመሪያ phase Review meeting ግምገማ ነው።
የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ሕ/ሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሲሆን ‘Resolve to save life Ethiopia’ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በክልሉ ዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ድንገተኛ ክስተቶችን በአግባቡ በመቃኘት፣በጊዜ በማሳወቅና ምላሽ በመስጠት የህ/ሰባችንን ጉዳት የመቀነስ አቅም ማሳደግ እንዲሁም በጤና ተቋማት ውስጥ ልከስቱ የሚችሉትን የተላላፊ በሽታዎች መተላለፊያ መንገዶችን በማስወገድና በመቆጣጠር ረገድ ይህ ድርጅት ትልቅ ውጤት እንድመጣ ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጿል ።
አክለውም በክልላችን ድንገተኛ ክስተቶችን ቀድሞ በመከላከልና ከተከሰቱም ፈጣን ምላሽ በመስጠት በርካታ ስራዎችን በመስራት እንደ ክልል አበረታች ዉጤቶች እንደተገኙ ገልፀዉ ይህንን ዉጤት አጠናክሮ ለማስቀጠል የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ተቋማትን አቅም የበለጠ ለማጠናከር ወሳኝ ፕሮጀክት በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ አካላት ለተግባራዊነቱ ተገቢዉን ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል።
በተጨማርም የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ በበኩሉ ፕሮጀክቱ ውጤታማ እንዲሆን በቀጣይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ጠቁሞ ቢሮውም በቀጣይ አብሮ እንደምሰራ ቃል ገብቷል ።
በአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ሙንጣሻ ብርሃኑ፣ ከኢንስቲትዩቱ እና ከከተማ ጤና ተቋማት ፣ Resolve to save life Ethiopia የPE የፕሮግራም ኃላፊዋ ወሮ ምንትዋብ ገ/እግዚአብሔር፣ የ ERPHC senior manager አቶ አሮን መብራቱ ፣ የክልሉ ERPHC program ተክንካል ማናጀር አቶ ተመስገን ንጉሴ ፣ የወረዳና ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዞን ጤና ደስክ አስተባባሪዎች እና የሆስፒታል መንተሮች እንዲሁም ጉዳዪ የሚመለከታቸዉ አካላት ተሳትፈዋል።
የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ታህሳስ 10/2017 ዓ.ም
ሀዋሳ
- by admin
- on December 23, 2024
0