Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የክልል ላቦራቶሪዎችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችል አንድ ቢሊዮን የሚጠጋ ብር ወጪ ተደርጎ የተገዙ የላብራቶሪ መሳሪያዎች ርክክብ መርሃ-ግብር ተካሄደ::


ለክልል ላበራቶሪዎች አቅም ግንባታ አገልግሎት ላይ የሚውሉት እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የላብራቶሪ መሳሪያዎቹ ኤልኢዲ ማይክሮስኮፖችን እና ማቀዝቀዣዎችን ጨምሮ በአይነት 39 ሲሆኑ፤ ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ የተገዙ ናቸው፡፡

ጠንካራ የጤና ስርአት ለመመስረት በዘመናዊ መሳሪያዎች የተደራጀ ላብራቶሪ ለጤናው ዘርፍ የጀርባ አጥንት መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በርክክብ መርሃ-ግቡሩ የተናገሩ ሲሆን፤ ጤና ሚኒስቴር በሽታ መከላከል፣ መቆጣጠር፣ ቅድመ ቅኝት ማድረግ እና ምላሽ መስጠት ዋነኛ ተግባሩ በመሆኑ ለዚህ ትልቁ አቅም ደግሞ ዘመናዊ ላብራቶሪዎችን ማደረጃት መሆኑን ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሃል ሃገር ብቻ ተወስኖ የነበረውን የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪ አገልግሎት በክልሎችም በማስጀመር ናሙናዎችን እዛው በክልል እንዲመረመሩ የሚያስችል አቅምን የፈጠረ ድጋፍ ነው ያሉት ዶ/ር መቅደስ፤ አሁንም ጤና ሚኒስቴር ተጨማሪ 14 የክልል ላብረቶሪዎችን በመገንባት፤ በሰው ሃብት እና በመሳሪያ እንዲሟሉ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የማይበገር የጤና ስርአት ለመገንባት የላብራቶሪ አቅምን በማሳደግ ወረርሽኞችን መከላከል ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፤ የተደረገው ድጋፍ የጤና ባለሙያዎችን አቅም የሚያሳድግ እና በክልል የተገነቡ ላብራቶሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ድጋፉን ያደረገውን የአለም ባንክን በተገልጋዩ ማህበረሰብ ስም ምስጋናም አቅርበዋል፡፡

የህብረተሰብ ጤና ላብራቶሪዎች አለም አቀፍ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲካሄድ መንግስት እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሃይሉ የገለጹ ሲሆን፤ ኢንስቲትዩቱ በሁሉም ክልሎች የሪፈረንስ ላብራቶሪዎችን በማቋቋም አገልግሎት እንዲሰጡ በመሳሪያ እንዲደራጁ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም ጥረት ከ50 በላይ ላብራቶሪዎች አለም አቀፍ አክሪድቴሽን/እውቅና እንዳገኙም አክለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስትትዩት የጤና ላቦራቶሪ አገልግሎት ዘርፍ ምክ/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሮ አብደላ በበኩላቸዉ ዛሬ ድጋፍ የተደረጉ ዘመናዊ የላቦራቶሪ ማሳሪያዎች የክልል ለቦራቶሪዎችን አቅም ለማጎልበት የሚዉል ሲሆን ነባር 19 የማይክሮ ባዮሎጂ ላቦራቶሪዎችን ለማጠናከር እንድሁም 15 አዳዲስ ላቦራቶሪዎች የማይክሮ ባዮሎጂ አገልግሎት እንዲጀምሩ ያስችላል ብለዋል።

ከላብራቶሪ መሳሪያዎቹ በተጨማሪም የክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቶች እና ድንበር ተሻጋሪ በሽታዎች ቁጥጥር የሚያገለግሉ 25 ሚልዮን ብር ወጪ የተደረገባቸዉ 52 የሞተር ሳይክሎችም ድጋፍ ተደርጓል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: @FMoHealthEthiopia
Tiktok: moh Ethiopian

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *