ስለ ማርበርግ በሽታ ይወቁ እራስውን ይጠብቁ!

Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.



የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ የመድረኩን ዓላማ እና የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን መንፈቅ አፈጻጸም አስመልክተው ሰፊ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት አመራርና ማኔጅመንት አባላት፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያዎች ፣ የሆስፒታሎች IDSR ተወካዮች ፣ አጋር ድርጅቶችና ጥሪ የተደረገላቸው የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ናቸው። በመድረኩም በበጀት ዓመቱ…

በጤናው ዘርፍ ለውጤታማ ውሳኔ ሰጪነት ትክክለኛ የጤና መረጃ መኖር ቁልፉን ሚና እንደሚጫወት ተገለጸ፡፡ ዶክተር ሊያ ታደሰ የጤና ሚኒስትር የመሠረታዊ የበሽታ ጫና አሰራሮች ስልጠና መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ትክክለኛ የጤና መረጃ መኖር በጤናው ዘርፍ ለሚኖረው ውጤታማ ውሳኔ ሰጪነት የሚጫወት ሚና እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ዶክተር ሊያ አያይዘውም የበሽታዋችን ጫና ለመቀነስ መረጃዎችን በመጠቀም ውጤታማ የጤና ውሳኔዎችን…

*//* ዛሬ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ ልዩ የደስታና የድል ብስራት ቀን ነው! ዳግማዊ አድዋ የሆነው የኢትዮጵያዊያንን የዘመናት ቁጭት ታሪክ የለወጠው ብሎም አዲስ የተስፋ ብስራትን ለትውልዱ ያበሰረው የሕብረብሔራዊ አንድነትና ፅናታችን መገለጫ የሆነው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በመመረቁ ታላቅ ኩራት እና ደስታ ይሰማናል! እንኳን ደስ አለን! እንኳን ደስ አላችሁ! የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጳጉሜ 4/2017 ዓ/ም ሀዋሳ ተጨማሪ መረጃዎች…


የሲዳማ ብ/ክ/መ/ጤና ቢሮ ፤ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም በሀገርቱ ከተፈጠረው የአየር ንብረት መዛባት ጋር በተያያዘ በክልላችንም በአንዳንድ አከባቢዎች የወባ በሽታ ጫና እየተፈጠረ ስለሚገኝ የመከላከሉን ስራ ከወራት በፍት ተጀምሮ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በዚሁ መሠረት በዛሬው ዕለትም በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን በሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ውኃን ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን (የአከባቢ ቁጥጥር ) ሥራ በሕዝብ ንቅናቄ ተደርጓል። በህዝብ ንቅናቄ ላይ…

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሆስፒታል ለተወጣጡ ለላቦራቶሪ ባለሙያዎች የላቦራቶሪ ጥራት ለማሻሻል ”SLMTA(Strengthening Laboratory Managment Toward Accreditation)” በሚል ርዕስ ከጥር 13/2018ዓ/ም ጀምሮ ስሰጥ የነበረ ስልጠና ተጠናቀቀ። በኢንስቲትዩቱ የላቦራቶሪ ዳ/ዳይሬክተር አቶ አዳቶ አዴላ በአጠቃላይ ውይይት እንደገለጹት በክልላችን ውስጥ የምገኙ ሆስፒታሎች በሙሉ SLMTA በመተግበር የላቦራቶሪ ጥራት እንዲያሻሽሉ እንደተደረገ እና በዚህ አመት አዳድስ ተቋማት ወደ ISO 15189:2022 እውቅና የምመጡ…