የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የብልጽግና ሕብረት አባላት “በምርጫ ማግስት፤ጠንካራ መንግስት” በሚል መሪ ቃል ወይይት እያካሄዱ ይገኛሉ።

ሀዋሳ||ሰኔ 9/2018 ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

መድረኩ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ሂደት እና በድህረ ምርጫ ሥራዎች ውጤት ላይ ያተኮረ ሲሆን የምርጫ ሂደቱን አጠቃላይ አፈጻጸም ለመገምገም እንዲሁም ምርጥ ልምዶችን ለመውሰድና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ የጋራ አቋም ለመያዝ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ እንደገለጹት የመድረኩ ዋና ዓላማ እስካሁን የተከናወኑ የምርጫ ሥራዎችን መገምገም እና ከምርጫ በኋላ የሚከናወኑ ተግባራትን በተቀናጀ መልኩ በማቀድ ወደ ትግበራ ለመግባት ነው ብለዋል።

ምርጫው የተመራበት ስኬታማ መንገድና ድል በምርጫው ማግስት የሕዝባችንን ሁለንተናዊ እርካታና ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ በሚያረጋግጥ መልኩ በቁርጠኝነት የምንተገብርበት ይሆናል በማለት ተናግረዋል።

የኢንስቲትዩቱ የፓርቲው አባላትም የ7ኛውን አገር አቀፍ ምርጫ ክልላዊ አፈፃፀም እየገመገሙ ይገኛሉ።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ስኔ 9/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *