በአፍሪካ ስለተከሰተው ኢቦላ ቫይረስ በሽታ እና በኢትዮጵያ እየተደረጉ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
ግንቦት 17 ፣ 2018 ዓ.ም
የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) በግንቦት 09 ፣ 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ (DRC) እና በዩጋንዳ በቡንዲቡግዮ (Bundibugio) ቫይረስ ዝርያ የሚመጣ የኢቦላ ቫይረስ በሽታ መከሰቱን ያሳወቀ ሲሆን እስከ ትላንት ግንቦት 16፣ 2018 ድረስ በእነዚሁ ሀገራት በአጠቃላይ ከ101 በላይ የሚሆኑ በላቦራቶሪ የተረጋገጡ ታማሚዎች እና ከ900 በላይ ንክኪ ያላቸው ተጠርጣሪዎች የህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
የኢቦላ ቫይረስ በሽታ ከፍተኛ የስርጭት እና የሞት ምጣኔ ያለው በሽታ ሲሆን ከሰው ወደ ሰው በንክኪ በቀላሉ ይተላለፋል።
እስከዛሬ ድረስ በሃገራችን ኢትዮጵያ ምንም አይነት በኢቦላ ቫይረስ በሽታ የተጠረጠረ ወይም የታመመ ሰው አልተገኘም።
ምንም እንኳን በሽታው ከተገኘባቸው አገራት ጋር ቀጥተኛ የድንበር ግንኙነት ባይኖረንም የበሽታውን አደገኛነት በመገንዘብ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) እና የአፍሪካ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ማዕከል (Africa CDC) የወረርሽኙን መከሰት ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ፦
– በሁሉም አለም አቀፍ የየብስ መግቢያ እና መውጫ ኬላዎች የልየታ እና የቅኝት ስራዎች በማጠናከር ፣
– በአለም አቀፍ አየር ማረፊያዎች የተጠናከረ ክትትል በማድረግ ፣
– የጤና ተቋማት ዝግጁ በማድረግ እንዲሁም የላቦራቶሪ አቅምን በማሳደግ
– እንዲሁም አስፈላጊው የህክምና ግብአት አቅርቦት ላይ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እየተከናወነ ይገኛል።
Website: ephi.gov.et
See less







