ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በክልሉ መንግስት ለሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የአምቡላንስ መኪና እና 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ
ሜሪጆይ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የኩላሊት እጥበት ህክምና መስጫ ማዕከል አስመረቀ። የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የኢፌዲሪ ጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ናቸው የኩላሊት እጥበት ማዕከሉን መርቀው በይፋ ስራ ያስጀመሩት። በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የማዕከሉን ባለራዕይ እና መስራች ያላቸውን የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ…









