ዘንድሮ በ2015 ዓ.ም የክረምት በጎ ተግባር ላይ
ከተሰሩ ስራዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልል ሤክተር መ/ቤቶች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሠርተፊኬት ተሽላሚ በመሆኑ!! እንኳን ደስ አላችሁ/አለን!!!
Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.

ከተሰሩ ስራዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በክልል ሤክተር መ/ቤቶች 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሠርተፊኬት ተሽላሚ በመሆኑ!! እንኳን ደስ አላችሁ/አለን!!!

ህዳር 28/2016 ዓ.ም የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ጤና አገልግሎት መምሪያ ዋና ኃላፊ ዶ/ር ኮማንደር አብርሃም ተፈራን እና የመምረያ ኃላፊዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን ጎበኝተዋል። የጉብኝቱ ዓላማ የልምድ ልውውጥ እና በቀጣይ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተቀናጅቶ በጋራ ለመስራት ነው። በመጨረሻም በቀጣይም ወረርሽኖችን ለመከላከል፣የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት፣ በህክምናና ድንገተኛ አደጋዎች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

“በጥናትና ምርምር የታገዘ ሥራ ውጤቱ ከፍተኛ ነው” – ዶክተር ዳመነ ደባልቄ በደረጀ ጥላሁን የሳምንቱ እንግዳችን ዶክተር ዳመነ ደባልቄ ይባላሉ፡፡ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡ ትውልድና እድገታቸው በሲዳማ ክልል ደበባዊ ዞን ሁላ ወረዳ ነው፡፡ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሀገረ ሰላም ከተማ ተምረዋል፡፡ ከ1996 ዓ/ም ጀምሮ በጤና ባለሙያነት፣ በጤና መምህርነት እና ጤና…

በዛሬው ዕለት በአፍ የሚሰጠው የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ተፈሪ ኬላ ከተማ በደራ ኦቲልቾ ወረዳ የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ዶ/ር ደረጃ ድጉማ፣ የኢትዮዽያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ እና ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጌታቸው ቶሌራ፣ የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደሪ፣ የወረዳው ጤና ቢሮ ም/ል ሀላፊ፣ የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብየሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት…

ኮሌራ በአይነምድር እና ትውከት ውስጥ በሚገኙ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን ፤ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ ኮሌራ በአይነምድር እና ትውከት ውስጥ በሚገኙ በአይን በማይታዩ ተህዋሲያን አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን ፤ በሰውነት ውስጥ የሚገኘውን ፈሳሽ አሟጦ በማስወጣት አቅምን የሚያዳክም በሽታ ነው፡፡ አፋጣኝ ሕክምና ካልተደረገ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በነፃ የስልክ መስመር፡ É7794 …

የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ እና የሻሎም ሄልዝኬር ሶልሽን ኩባንያ መስራችና ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊንታ መሃሪ የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻ ፋብሪካ ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ በማስቀመጥ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂደዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለፁት በጤና ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ለህክምና የሚያስፈልግ ግብዓት ማግኘት ከባድ በመሆኑ ዜጎች ህይወታቸው አደጋ ውስጥ ሲጥል ቆይቷል በማለት ይህ ፋብሪካ ይህን ችግር…

በሲዳማ ክልል ጤና ሰክተር “ለውጤት እንስራ” በሚል መሪ ሀሳብ በቢሮው የተጀመረውን አጠቃላይ የጤና ስራን ለሚገመግም ሱፐርቭዥን ቡድን ኦሬንተሽን የተሰጠ ሲሆን የስምሪት መድረኩን የመሩት የክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅፅ/ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፊ ኃላፊ አቶ አስፋው ጎነሶ እንደተናገሩት ጤናማና አምራች ህ/ሰብ በመገንባት የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት እንዲቻል በዚህ ዘርፊ ያለውን አጠቃላይ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱ የሚመራበትን ሂዴት በጥልቀት…

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ በሀዋሳ ከተማ ለ100 ሁለገብ ባለሙያዎች የአንድ ወር ስልጠና ከፈቱ። ስልጠናው በ24 – 48 ሰአታት ውስጥ በድንገተኛ አደጋዎች ለመሰማራት ዝግጁ የሆኑ በደንብ የሰለጠኑ፣ የታጠቁ፣ ቀልጣፋ እና ተለዋዋጭ ባለሙያዎችን ዝርዝር በማዘጋጀት ለጤና ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት ምላሽ ሰጪ ቡድኖችን ማጠናከር እና መጠቀም ላይ ያተኩራል። ስልጠናው የኢፒአይአይ ከጤና ጥበቃ…

በጤና ቢሮ እና በተጠሪ ተቋማት እያገለገሉ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት ሥር የሚገኙ አመራር እና ሰራተኞች በፓርቲው የዘጠኝ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። በተያያዘም በዚሁ ሪፖርት ተለይተው የወጡ ጉድለቶችን ለመሙላት ዛሬ የተደረገው ውይይት ለፓርቲው አባላት የበለጠ አቅም እንደሚፈጥርና ሁሉም አመራርና አባላት ተቀራራቢ የሆነ አቋም እንዲኖራቸው ያስችላል ተብሎም ይጠበቃል። በኮንፈረንሱ በስራቸው የተሻለ ዉጤት…

በ2030 የወባ በሽታን ለማስወገድ የተቀመጠዉን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ ሳይንሳዊ የምርምር ኔትዎርክ ሲምፓዚየም በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን በሲምፓዚየሙ ላይ የተለያዩ ጥናትና ምርምር ዉጤቶችና ግኝቶች ቀርበዉ ዉይይት ይደረግበታል። በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘዉ 13 ኛዉ የወባ ሳይንሳዊ ምርምር ኔትዎርክ ሲምፖዚየም መክፈቻ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የወባ በሽታ በገዳይነቱ ብቻ ሳይሆን በመኸር…