ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በሲዳማ ክልላዊ መንግስት የሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የስራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ ።
በልምድ ልውውጡ በክልሉ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዮት እየተተገበረ ያለውን የመረጃ አያያዝ /ዳታ ማናጅመንት ሲስተም ፣ የነፃ ስልክ ጥሪ ማእከል (call centre) ፣ የሕብረተሰብ ጤናና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር (PHEM) ፣ የክልል ላቦርቶሪ (Regional Laboratory) እና የሕብረተሰብ ጤና ምርምር ስራዎች ላይ የገለጻ እና የአካል ምልከታ በማድረግ የእርስ በዕርስ የአሰራር ልምዶችን በመለዋወጥ በጤናው ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት እና ቅልጥፍና…










