በማንኛውም የዕድሜ ክልል ውሰጥ የሚገኙ ሰዎች ሰዉነትን ያዳረሰ ሸፍታ እና ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት በተጨማርም ሳል ወይም የንፍጥ መዝረብረብ ወይም የዓይን ህመም (መቅላት) ሲኖር የኩፍኝ በሸታ ሊሆን ሰለሚችል ፈጥነው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን ህክምና ያግኙ።
ለበለጠ መረጃ በነፃ የሰልክ መሰመር 7794 ይደውሉ!! በሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.

ለበለጠ መረጃ በነፃ የሰልክ መሰመር 7794 ይደውሉ!! በሲዳማ የሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የካንሰር ህክምና ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጫ ማዕከላት ተመረቁ ። የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ፣ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በየነ በራሳ እንዲሁም የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አያኖ በራሳ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ማዕከሉ በዛሬው እለት ተመርቋል። የካንሰር ጨረራ ህክምና ማዕከል ፤…

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በማጠቃለያ መድረክ ላይ ባስተላለፉት መልዕክታቸው ስልጠናው አንድ የጤና አመራር /ባለሙያ ሊጠብቀውና ሊተገብረው የሚገባውን ወሳኝ የሆኑ የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን አውቆ እንዲተገብር የሚያስችል ነው። ከዚህ አኳያም ባለፉት ሶስት ቀናት የተሰጠው ስልጠና ውጤቱ ቀጥሎ በእያንዳንዱ መዋቅር ደረጃ በሚኖረው አፈጻጸም የሚለካ ሆኖ ሰልጣኙ ወደ መደበኛ ሥራ ቦታቸው ሲመለሱ ከዚህ በፍት ከነበረው በተሻለ ሁኔታ…

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አብርሃም ማርሻሎ በንግግራቸው ከሁለት ዓመት በፍት በጤና ሴክተር ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የሚያያዙ ፣ የግብዓት አቅርቦት ፣ አያያዝ እና መሰል ችግሮች እንደነበሩ ገልጸው የጤና ቢሮው አመራሮች ቆም ብለው የችግሩን ምንጮችና የመፍትሄ አቅጣጫን መቀየስ በመቻላቸው በአሁኑ ጊዜ በሴክተሩ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል :: ኃላፊው…

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፕሮጀክቱን ወደ ሲዳማ ክልል አውርዶ ለመስራት ግንቦት 22 /2016 ዓ.ም በሀዋሳ በተዘጋጀው ወርክሾፕ ላይ የጋራ ስምምነት ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር መሳይ ኋይሉ በስምምነቱ ላይ እንደናገሩት ፕሮጀክቱ ከስርዓተ – ምግብ ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን ችግር በምርምር ለመፍታት የሚሰራ ሲሆን ኢንስቲትዩቱ የተቀበለውን ሃላፊነት በተሻለ ደረጃ እየተወጣ እና ወደ ክልሎች ለማድረስ…

ሳምንታዊው የጽዳት ዘመቻውን ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፍ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ሲሆኑ ዛሬ የሚደረገው የጽዳት ዘመቻ ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት በሳምንቱ መጨረሻ አርብ አርብ ይደረግ የነበረው ዘመቻ መሆኑን ገልጸዋል። የጽዳት ዘመቻውን በተመለከተ የቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ንግግር አድርገው ያስጀመሩ ሲሆን በመልዕክታቸውም የዛሬውን የጽዳት ዘመቻ ለየት የሚያደርገው ቁርኝታችንን እና አንድነታችንን ባጠናከረ መልኩ የጤና ስራ…


የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር የተከበሩ አቶ መስጠፌ ሙሐመድ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ በክልሉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ምላሽ ከሁሉም በላይ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ተግባራት አንዱ እንደሆነ ጠቁመዋል። የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር የተከበሩ ዶ/ር መቅደስ ዳባ የተከስቱትን እና ሊከሰቱ የሚችሉ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየደረጃዉ የምትገኙ ሚኒስትሮች ፣ ሚኒስቴር ድኤታዎች ፣ የክልል ፕሬዘንዳቶች ፣…

ንፅህና ለህብረተሰብ ጤና ስርዓት ያለው ሚና የጎላ በመሆኑ “ለፅዱ ጎዳና ኑሮ በጤና” ጥሪ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል ሲሉ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገለፁ፡፡ “ጠንካራ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ለማይበገር የጤና ስርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የህብረተሰብ ጤና አደጋ ምላሽ ማሻሻያ ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል። በመድረኩ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ…

የሞዛምቢክ መንግሥት ጤና ሚኒስቴር እና የሞዛምቢክ የአለም ጤና ድርጅት አባላትን የያዘ የልዑክ ቡድን በሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር ላይ የልምድ ልውውጥ ለመውስድ ወደ ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል። በዕለቱ እንኳን በደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና እንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄኔራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ ሲሆን አጠቃላይ በተቋሙ ደረጃ እየተስሩ ያለ ስራዎች ገለፃ በማድረግ…