ከትግራይ ክልል ጤና ምርምር እንስቲትዩት ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተወጣጡ ዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች በሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የስራ ልምድ ልውውጥ አደረጉ።
የልምድ ልውውጥ ቡድን አባላትን እንኳን በደህና መጣችሁ በማለት መግቢያ ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሲሆኑ በክልሉ እየተተገበረ ያለውን የመረጃ አያያዝ /ዳታ ማናጅመንት ሲስተም ፣ ነፃ የስልክ ጥሪ ማእከል (free call center) ፣ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፣ የክልሉ ላቦርቶሪ እና ጤና ምርምርና ተክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ላይ ገለጻ…










