የህዝብ ክብረ በአላትን በሚያከብሩበት ጊዜ ራስዎን ይጠብቁ!
ህዝብ በሚሰበሰብበት ወቅት የኢንፌክሽን አደጋዎችን ለመቀነስ ተግባራዊ መመሪያ #MarburgVirus
Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.

ህዝብ በሚሰበሰብበት ወቅት የኢንፌክሽን አደጋዎችን ለመቀነስ ተግባራዊ መመሪያ #MarburgVirus

የአፈጻጸም ግምገማው መድረክ ተሳታፊዎች ሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ ሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ፣ ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት እና ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ አጋር ድርጅቶች ሲሆኑ ፧ በክልሉ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረሰ በሽታ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በየዕለቱ የተተገበሩ ተግባራት ሪፖርት በሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዝርዝር ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት ተደርጓል ። በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ…

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ህዳር 20/2018 ዓ.ም የጤና ሚኒስቴር ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በየደረጃው ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎችና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በማርበርግ ቫይረስ በሽታ ላይ ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ታውቋል። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በመልዕክታቸው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጂንካ ከተማ መከሰቱ ከታወቀበትና በነበረው ቀጥተኛ…

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ህዳር ,20/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፣ከሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ፣ከጤና ሚንስተር ፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በክልሉ የተከሰተውን የማርበርግ ቫይረስ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀውስ አሰተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት እየተሰሩ ያሉ ፈጣን የምላሽ ተግባራትን በክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል (EOC) የግምገማ መድረክ…

#MarburgVirus የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት ህዳር 19/2017 ዓ.ም ሐዋሳ ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794 Web site: https://sphi.gov.et/

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት 19/2018 የጤና ሚኒስቴር ለሲዳማ ክልል የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከልና ቁጥጥር የሚውሉ አስፈላጊ ቁሳቁሶችንና አንቡላንሶችን የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ርክብክብ አድርጓል። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር አቶ ደስታ ሌዳሞ ድጋፉን በተረኩቡበት ወቅት እንደተናገሩት የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጂንካ ከተማ መገኘቱ…

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የማርበርግ ቫይረስ (Marburg virus) በማንኛውም ንክኪ መተላለፍ የሚችል እጅግ በጣም አደገኛ በሽታ በመሆኑ የገጻችን ተከታዮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን። ከማንኛውም መነካካት (መጨባበጥ) እንዲቆጠቡ በመደበኛነት የእጅ ሳኒታይዘር እንዲጠቀሙ ማንኛውንም ነገር ከነኩ በኋላ እጆችን በሚገባ እንዲያጸዱ እንመክራለን! ሰው በሚበዛባቸው እና ከፍተኛ መነካካት በሚያስከትሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። #MarburgVirus የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት ህዳር 18/2017 ዓ.ም ሐዋሳ…

#MarburgVirus የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት ህዳር 17/2017 ዓ.ም ሐዋሳ ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794 Web site: https://sphi.gov.et/

************* የማርበርግ በሽታ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የበሽታውን አሁናዊ ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። በሽታው መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የክትትልና የልየታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑ በመግለጫው ተመላክቷል። በመሆኑም እስከ ዛሬው እለት የተለያዩ ምልክቶች ታይቶባቸው 73 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው 11 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል። ከእነዚህም ውስጥ 6…

————————– (ዜና ፓርላማ) ሕዳር 17 ፣ 2018 ዓ.ም፤ የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስተውቋል። ቋሚ ኮሚቴው ኢንስቲትዩቱ በህብረተሰብ ጤና ላይ የሚደርሱ የጤና አደጋዎችን ለመከለከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል መረጃን በማጠናቀር እንዲሁም የጥናትና ምርምር ተግባራትን በማከናወን በጤናው…