ኤም ፖክስ
#Mpox
Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.


የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በክልሉ ደረጃ በመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዙሪ ቁልፍ አጀንዳ ተደርጎ በነበሩ ”ለውጤት እንስራ እና ለላቀ ውጤት እንስራ ” ኢንሼቲቮች የታደሱ ጤና ተቋማትን በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የሚመራ ቡድን ጉብኝት አደረጉ ። የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 13/2017 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ጤና…

በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዓለም አቀፍ የጤና ደንብ እና የአንድ ጤና ፅ/ቤት፣ ከሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ አለም አቀፍ የጤና ድርጅት እና ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር የሲዳማ ክልል የጤና ደህንነት አቅም ለማጠናከር የሚያስችል የግምገማ አውደ ጥናት ከሰኔ 4 እስከ 6 /2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው:: የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ስራዎችን በሚገባ ተግባራዊ…

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሰኔ 5/2017 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና የጤና ተግባቦት ስራዎችን ማጠናከር ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ከዞንና ከወረዳ የጤና ትምህርት ባለሙያዎች ጋር አካሂዷል። የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ሀላፊ አቶ በላይነህ በቀለ በመልዕክታቸው የማህበረሰቡን የበሽታ ተጋላጭነት ለመቀነስና ጤናማና አምራች ዜጋ የመፍጠር ራዕይን እውን ለማድረግ የማህበራዊ ባህሪ ለውጥ ተግባቦት…


የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ጋር በመተባበር የሴቶችን የውሳኔ ሰጭነት ለማሳደግ የስልጠና እና የምክክር መድረክ ተካሂዷል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ህዝብ ግንኙነት ዳይረክቶረት ሰኔ 03/2017 ዓ.ም በዕለቱ እንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ምትክል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ ስሆን በውሳኔ አሰጣጥ ዙሪያ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እና ትኩረት የሚሻ ጉዳይ በመሆኑ ከጊዜ…

በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ በሽታ (Mpox) መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተር ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በሲዳማ በክልል የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ። በዚሁ መነሻ በክልሉ ለሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች ሙያዊ እና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የመከላከል ስራውን አጠናክረን በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በመክፈቻ ንግግራቸው ጥሪ…

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲተትዩት ግንቦት 27/ 2017 ዓ.ም በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ በሽታ/ Mpox መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተርና ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በክልሉ የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸውን የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት አሳውቋል። የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በመክፈቻ ንግግራቸው የ ኤም ፖክስ (Mpox)በሽታ በዓለም…

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ውስጥ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ( MPox) መከሰቱን ከጤና ሚኒስቴር – ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ከሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መግለጫ መሰጠቱ ይታወቃል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩትም በበኩሉ ወረርሽኙ ከተከሰተበት ዕለት ጀምሮ በሁሉም መዋቅሮች ጠንካራ የቅኝት ስራ በመሥራት ላይ ይገኛል። የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሲዳማ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር ሕብረተሰቡ በመተላለፊያ መንገዶቹ ላይ ማለትም፦በበሽታው ከታመመ ሰው…

በክልሉ ሰሜናዊ ዞን ሸበድኖ ወረዳ ድላ አፋራራ ቀበሌ ክልላዊ የማስጀመሪያ መረሐ ግብር ላይ ተገኝተው ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዋ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበጀት አመቱ በክልሉ የመጀመሪያው ዙር የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የተሳካ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ፡፡ አክሎም እንደገለፁት ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግና መከተብ ያለባቸውን ህፃናት በሙሉ እንዲያስከትቡ አሳስበዋል። በክልሉ ከአንድ ሚልየን በላይ ህጻናት…