Resolve to Save Lives የሚባል መንግሰታዊ ያልሆነ ድርጅት በሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ስር ለሚገኙ 23 ጤና ጣቢያዎች ከ4.6 ሚልዮን ብር በላይ የሚገመት የተለያዩ ቆሻሻ ማሰባሰቢያ ባልዶችን፣ የወለል ማጽጃ ዕቃዎችን ፤ የለይቶ ማከሚያ አልጋዎችን፣ የሙቀት መለክያ መሳሪያዎችን እንዲሁም የተላላፊ በሽታ መከላከያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የጤና ቢሮ ኃላፏ ዶ/ር ስላማዊት መንገሻ፣ የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ እንዲሁም የRTSL ፕርንስፓል ማናጀር ወ/ሮ ምንትዋብ ገ/እግዚአብሔር ተገኝቷል።
የሲዳማ ሕብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጥር 17,2017 ዓ ም
ሀዋሳ









