እንኳን ለሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ -ጨምባላላ በዓል በሠላም አደረሰን/አደረሳችሁ !!
Fichee Jeeji Jeeji !!
Get the latest public health alerts and emergency updates from Sidama Public Health Institute.

Fichee Jeeji Jeeji !!

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሀምሌ 30፣ 2018 ዓ.ም. ከዓለም አቀፉ ጌትስ ፋውንዴሽን የተውጣጡ ከፍተኛ ልዑካን በሲዳማ ክልል እየተተገበረ ያለውን የድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ (Public Health Emergency Management-PHEM) ሥርዓት በመጎብኘት የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል። ልዑካኑን የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በቢሯቸው ተቀብለው ስለ ክልሉ የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ…
በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ አሰጣጥ (Evidence-Informed Decision-Making – EIDM) ጉባኤ በአድዋ ሙዚየም አዳራሽ እየተካሄደ ሲሆን የጤና ስርዓቶችን በዕውቀት፣ በማስረጃና በትብብር ማጠናከር የወቅቱ ቁልፍ አጀንዳ መሆኑ ተገለጸ። በጉባኤው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ኃይሉ፣ ጉባኤው የጤና ስርዓቶችን በዕውቀት፣ በማስረጃና በትብብር ለማጠናከር ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንፀባርቅ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። ዶክተር መሳይ…

የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት መጋቢት 28 ቀን 2017 ዓ.ም በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ በመገኝት ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ጤና እንስትቲዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ሪዞልቭ ቱ ሴቭ ላይቭስ /Resolve to Save Lives/ለወረርሽኝ ምክንያት የሚሆኑ በሽታዎችን አስቀድሞ በመከላከል እና ዝግጁነት ላይ በ15 ወረዳዎች እና በ3 ከተማ አስተዳደሮች በሚገኙ 50 የመንግሥት ጤና…


ጥር 30/2017 ዓ.ም ፤ ሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በሀገር ደረጃ በየአመቱ የሚካሄደው የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ፎረም ሲካሄድ የቆየ ሲሆን 10ኛው ደግሞ በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል። ፎረሙን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አየለ ተሾመ በንግግራቸው ፥ ባለፉት ጊዜያት አለማችን ብሎም ሀገራችንን ጤና የሚፈታተኑ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ ድንገተኛ…

በሀገራችን ኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ የኤም ፖክስ በሽታ (Mpox) መገኘቱን ተከትሎ የጤና ሚኒስተር ባስተላለፈው መልዕክት መነሻነት በሲዳማ በክልል የተጠናከረ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ። በዚሁ መነሻ በክልሉ ለሚገኙ መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች ሙያዊ እና በገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የመከላከል ስራውን አጠናክረን በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በመክፈቻ ንግግራቸው ጥሪ…