
Similar Posts

የኮሌራ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባው ተገለጸ
Byadmin————————- ባለፉት አምስት አመታት በአፍሪካ ቀንድ አገራት ከኮቪድ ወረርሽኝ ባሻገር ወቅታዊ በሆኑ ተፈጥሮአዊ እና ሰዉ ሰራሽ አደጋዎች ተፅዕኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህም ዉስጥ ከድርቅ ጋር ተያይዞ የሚመጡ አጣዳፊ የስነ-ምግብ እጥረት፣ ኮሌራ እና ሌሎችም ተላላፊ በሽታዎች ወረርሽኝ ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡ ስለሆነም የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከክልል ጤና…

ስለ ማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች
Byadmin#MarburgVirus የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲዩት ህዳር 17/2017 ዓ.ም ሐዋሳ ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794 Web site: https://sphi.gov.et/
የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እና የአህጉራዊ አንድነት ተምሳሌት የሆነችው አዲስ አበባ፣ በጤናው ዘርፍ አህጉራዊ ታሪክ ያተረፈ ታላቅ ጉባኤ ከሰሞኑ አስተናግዳለች። ከመላው አፍሪካ (ከምዕራብ፣ ከምስራቅ፣ ከማዕከላዊ እና ከደቡብ) ከተውጣጡ 36 ሀገራት የመጡ የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የህዝብ ጤና ተቋማት መሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ አካዳሚክ ተቋማት እንዲሁም አለም አቀፍ አጋሮች በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል፡፡
Byadminይህ ታሪካዊ መድረክ “ካውንትዳውን 2030” (Countdown 2030) በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ አህጉሪቱ ወደ 2030 የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) የምታደርገውን ጉዞ ፍጥነትና ውጤታማነት በጋራ ለመገምገም የተዘጋጀ ነው። ቀደም ሲል በሚሊኒየም የልማት ግቦች (MDGs) ዘመን ተጀምሮ የነበረው ይህ ንቅናቄ፣ አሁን ላይ የአፍሪካ ሀገራት በጤናው ዘርፍ ያመጧቸውን ለውጦች፣ በተለይም የእናቶች፣ የጨቅላ ህፃናት እና የህፃናት ጤና አጠባበቅ ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና…
የካውንት ዳውን 2030 ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል
Byadmin———————- የዘላቂ ልማት ግቦችን (Sustainable Development Goals 2030 /SDG/) መነሻ በማድረግ በመላው አፍሪካ የሚገኙ የጤና መረጃዎችን፣ የእናቶች እና የህፃናት ጤና አፈጻጸምን ለመገምገም የተዘጋጀው “ካውንትዳውን 2030” (Countdown 2030) የተሰኘው አህጉራዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ከ36 የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ የጤና ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ ተመራማሪዎች እና የአለም አቀፍ…

የስኬት ዜና !
Byadminበዛሬው ዕለት (2/06/2018 ዓ.ም ) የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባዘጋጀው የእውቅና መስጫ ፕሮግራም ላይ ባለፉት ጊዜያት ፥ ማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝንና ሌሎችን ጨምሮ በሀገር እና በክልሎች ደረጃ የተከሰቱ ወረርሽኞችን ለመግታት በሲዳማ ክልል የሚገኙ የጤናው ዘርፍ ተዋናዮች ባሳዩት ቁርጠኝነት በህብረተሰብ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ በአጭር ጊዜ ወረርሽኞችን መግታት በመቻላቸው ፤ ለክልላችን ጤና ቢሮ ፣ ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በጎፋ ዞን፤ በገዜ ጎፋ ወረዳ፣ በኬንቾ ሻቻ ጎዚዲ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የተላከውን የመጀመሪያ ዙር የሰብአዊ ድጋፍ ቁሳቁስ ፣ መድኃኒት እና የድንገተኛ ህክምና ቡድን ያካተተ ድጋፍ የሚያደርስ በዶ/ር ዳመኔ ደባልቄ (የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ) እና በአቶ አበራ ዊላ (የሲዳማ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽኔር ) የሚመራ ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ስፍራው በማቅናት ላይ ይገኛል።
Byadminሐምሌ 18/2016 ዓ.ም


