Today, the Sidama Public Health Institute (SPHI) hosted a research workshop focused on strengthening evidence-based health interventions across the region. In his opening remarks, SPHI Director General Dr. Damene Debalke emphasized that scientific research and data-driven evidence are vital for driving progress and improving healthcare performance.

The session featured presentations on completed research alongside upcoming initiatives. Senior researcher Dr. Amelo Bolka presented study findings on the readiness of health professionals for digital health implementation in public hospitals. Following this, senior researcher and statistician Dr. Dereje shared a comprehensive multi-year analysis of reportable disease profiles from 2013 to 2024, examining regional trends, spatial distributions, and case fatality rates.

Expanding on future health priorities, Mr. Aschalew Arega outlined a 2026 research proposal investigating primary healthcare facility readiness for routine immunization delivery beyond basic vaccine supply. The workshop concluded with an interactive discussion moderated by SPHI Vice Director General Mr. Ougamo Hanaga, where presenters addressed audience feedback and key questions.

በዛሬው ዕለት የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (SPHI) በክልሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸው የጤና ችግሮች ላይ ያተኮረ የጥናትና ምርምር ወርክሾፕ አካሂዷል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዳመነ ደባልቄ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፣ በክልሉ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ጠንካራ ሳይንሳዊ ምርምርና አስተማማኝ መረጃዎች ወሳኝ ናቸው። የሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተሰጡት ተልዕኮዎች አንዱ በጥናትና ምርምር የጤና ችግሮችን በመለየት ለፖሊሲ የሚሆን መረጃን ማቅረብ ስለሆነ በሚቀጥሉት ጊዜያትም ጥናትና ምርምርን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በወርክሾፑ ላይ በተጠናቀቁ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን አንድ አዲስ የጥናት ፕሮፖዛል ቀርቧል፡፡ የኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር አመሎ ቦልካ የህዝብ ሆስፒታሎች ላይ የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎች የዲጂታል ጤና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ያላቸውን ዝግጁነት የሚያሳይ የጥናት ግኝት አቅርበዋል።

በመቀጠልም፣ ከፍተኛ ተመራማሪና ስታትስቲሻን ዶክተር ደረጀ ከ2013 እስከ 2024 (እ.ኤ.አ) በክልሉ የታዩ ዋና ዋና በሽታዎችን፣ የሥርጭት ሁኔታ እና፣ መልክአ-ምድራዊ ስርጭታቸውን እና የሞት ምጣኔያቸውን የሚያሳይ የጥናት ውጤት አቅርበዋል።

በቀጣይነት ሊሰራ የታቀደ ጥናትን ያቀረቡት ደግሞ ፣ አቶ አስቻለው አረጋ የጤና ተቋማት መደበኛ የክትባት አገልግሎት ለመስጠት ያላቸውን ዝግጁነት የሚመለከት የጥናት ፕሮፖዛል አቅርበዋል። ወርክሾፑ በኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በአቶ ኡጋሞ ሃናጋ መሪነት በተካሄደ የውይይት መድረክ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ፕሬዘንተሽን ያቀረቡት ተመራማሪዎች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሀምሌ 27/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *