የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት አበረታች ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገለጸ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ጳጉሜን 4/2018 ዓ.ም.

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 2018 በጀት ዓመት በድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ፣ ህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት ፣ በምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና በመረጃ አያያዝ ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑ ተገልጿል ።

በዛሬው ዕለት ኢንስቲትዩቱ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሙን የገመገመ ሲሆን፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዋና ዋና ግቦችንና የትኩረት መስኮችንም አስተዋውቋል ።

በመድረኩ የቀረበውን የአፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግም ከተሳታፊዎች ገንቢ አስተያዬቶች ከመሰጠታቸው ባሻገር አንዳንድ በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ተግዳሮቶችን እና በ2019 ዓ.ም ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት መደረጉም ታውቋል ።

በማጠቃለያ መድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ ፣ 2018 በጀት ዓመት የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጨምሮ በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ መሻሻሎችና ለክልሉም ሆነ ለሀገር ምሳሌ የሚሆኑ በርካታ ሥራዎች የተከናወኑበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል።

የተሻለ አፈጻጸም ከተመዘገበባቸው የስራ ዘርፎችን የቢሮ ኃላፊዋ ሲጠቅሱ ፥በድጂታላይዜሽን አተገባበር ላይ የታዩ ለውጦች ፥ የህብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ቴክኖሎጂ (ዲ. ኤች. አይ.ኤስ-2) አፈጻጸም ወደሚፈለግበት ደረጃ መድረሱ እንዲሁም ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በጤና ተቋማት ገብራዊ ማድረግ ፣ የህብረተሰብ ጤና የላብራቶሪ አገልግሎትን በዘመናዊ መሣሪያዎች ማሻሻል እና ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውን ምርመራዎች ማስጀመር እንዲሁም ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምር ስራዎች በዓመቱ ከተመዘገቡ ዋና ዋና ውጤቶች መካከል መሆናቸውን ዶ/ር ሰላማዊት ገልጸዋል ።

ኃላፊዋ አያይዘውም የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የውስጥ አቅሙን በማጎልበት ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን ለመግታት በተሠራው ሥራ በተለይ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝን ባጠረ ጊዜ በመከላከልና በመቆጣጠር ያሳየው ብቃት ለሀገሪቱም ተሞክሮ ሊሆን የሚችል አንደሆነ በአድናቆት አንስተዋል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ በበኩላቸው፣ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የሚከሰቱ የጤና አደጋዎችን ቀድሞ ለመለየትና ተገቢውን ምላሽ በፍጥነት ለመስጠት የቅኝትና የአሰሳ ሥራዎችን በማጠናከር በሽታዎች በሕብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሳያስከትሉ ባጠረ ጊዜ እንዲቆጣጠሩ ማስቻሉን ገልጸዋል። በታችኛው እርከን ያሉ መዋቅሮች ሪፓርታቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቅመው እንድልኩ ለማስቻል ከ110 በላይ ዘመናዊ ኮምፕተሮችን ለወረዳዎች እና ለጤና ተቋማት መሠራጨቱንም ጠቁመዋል።

በመድረኩ በበጀት ዓመቱ በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተጣሉ ግቦችን በአግባቡ የፈጸሙ እና የመሩ መዋቅሮች እና ግለሰቦች የዕውቅና ምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን ፤

የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ የዓለም አቀፍ የጤና ኢንስቲትዩቶች መስፈርት በማሟላት የሚፈለጉ ቅድመ – ሁኔታዎችን በሚፈለገው ደረጃ ማሟላት በመቻሉ ባሳለፍነው በጀት ዓመት በአስደናቂ ሁኔታ ውድድሩን በማሸነፍ International Association of National Public health Institute (IANPHI) አባል መሆን መቻሉን ምክንያት የቢሮ ኃላፊዋና የኢንስቲትዩቱ አመራርና ሠራተኞች በጋራ በመሆን ይህንኑ አስመልክቶ የተዘጋጀውን የኬክ ቆረሣ ተደርጎ ደስታቸውን አጣጥመዋል ።

በመድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮና የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማኔጅመንት አባላት ፣ የፌደራል ተቋማት ኃላፊዎች ፣ የዞንና የወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤት አስተባባሪዎችና ኃላፊዎች ፣ የኢንስቲትዩቱ ሠራተኞች፣ አጋር አካላትና እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ጳጉሜ 4/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *