የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አመራሮችና የብልጽግና ፓርቲ አባላት ሠራተኞች 3ኛ ዙር የአባላት ኮንፈረንስ አካሄዱ።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሚያዚያ 06/2018 ዓ.ም

በኮንፈረንሱ መድረክ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ባስተላለፉት መልዕክት ጠንካራ ሀገር ለመገንባትና የተጀመረውን ፈጣን ልማት ለማስቀጠልና ለማሳለጥ በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት የአባላት ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ክልል ኢንስቲትዩቱ የህዝቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ የሕብረተሰብ ጤና ስጋቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፣ የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አጠናክሮ ለማስቀጠል አባላት በግንባር ቀደምትነት በመሰለፍ የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አሁን ካለው ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ እና አገር አቀፋዊ ሁኔታ አንፃር በሀገራችን ጎን መቆም የሁሉም አባላት የጋራ ኃላፊነት በመሆኑ፣ ትውልዱ ለሀገር ፍቅር ኃላፊነት እንዲኖረው ማድረግ ከሁሉም አመራርና አባላት የሚጠበቅ ተግባር እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል።

በመቀጠልም ዋና ዳይሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ አባላትና ሠራተኞች በ 7ኛው ሀገር-አቀፋዊ ምርጫ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን የብልጽግና ፓርቲያችንን የበላይነት እንዲያረጋግጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የ9 ወር አፈጻጸም ያቀረቡት የጤና ኢንሰቲትዮት የብልጽግና ፖርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ዮኤል ዮኦላ ሲሆኑ በ9 ወራት ውስጥ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ በክፍተቶቹ ላይ በቀጣይ እርምት እንዲደረግ አሳስበዋል።

በቀረበው ሪፖርት መነሻ አባላት ባቀረቡት ሀሳብ፦ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሀሰት መረጃ በማሰራጨት፣ በአባሉና በአመራሩ መካከል ጥርጣሬና ግጭት እንዲፈጠርና የተሰራውን የልማት ሥራ ወደጎን በመተው ጥቂት በሚቀሩ ጉድለቶች ላይ ብቻ በማተኮር ተገቢ ያልሆነ ሀሳብ በሚያዘዋውሩ አካላት ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ሚያዚያ 6/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ መረጃዎች የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት:

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://www.sphi.gov.et/

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *