የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዲጂታል ጤና ላይ የሚሠራውን የጥናት ፕሮፖዛል ሴሚናር አካሄደ።

የሲዳማ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ግንቦት 26/2018 ዓ.ም

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዘወትር በየሁለት ሳምንት በሚያካሄደው መደበኛ የምርምር ሴሚናር ላይ “በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በመንግሥት ሆስፒታሎች የዲጂታል ጤና አተገባበር ዝግጁነት ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የምርምር ፕሮፖዛል በኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ተመራማሪ በዶ/ር አመሎ ቦልካ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የጥናቱ ዋና ዓላማው በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች ወደ ዲጂታል የጤና አሰራር ለመሸጋገር ያላቸውን ዝግጁነት፣ አቅምና ውስንነት በሳይንሳዊ መንገድ በመፈተሽ የጤና አገልግሎት አሠጣጥን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ እድገቶች ጋር ለማጣጣም ያለመ ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ በበኩላቸው ፤ ጥናቱ በጤናው ዘርፍ ለሚቀረጹ ፖሊሲዎችና የአሠራር ሥርዓቶች ሳይንሳዊ መረጃዎችን በማመንጨት ለውሳኔ ሰጪዎች ጠቃሚ ግብዓት እንደሚሆን ገልጸዋል።

በሴሚናሩ ላይ በጥናቱ ስልት (Methodology)፣ የመረጃ አሰባሰብ ሂደት እና ጥናቱ ሊያስገኝ በሚችለው ጠቀሜታ ዙሪያም ሰፊ ውይይት ተካሂዶ፤ ከተሳታፊዎች የቀረቡ አስተያየቶች ጥናቱን የበለጠ የሚያጠናከሩ በመሆናቸው በፕሮፖዛሉ ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ግንቦት 26/2018 ዓ/ም

ሀዋሳ

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች

👇👇👇👇 ይመልከቱ

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: sphi.gov.et/emergency

Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173

Telegram: https://t.me/c/1865772308/1

Email:- admin@sphi.gov.et

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *