Skip to content የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ፤ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም
በክልሉ ባለፉት ጊዜያት ከክልል ማዕከል ጀምሮ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ሲካሄድ የነበረው የ2016 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ በዛሬው ዕለት በክልሉ ጤና ቢሮ እና ለቢሮው ተጠሪ በሆኑ መ/ቤቶች ደረጃ የሚገኙ አባላትና ደጋፊ ፐብሊክ ሰርቫንት የውይይት መድረክ ተጀምሯል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክቡር ፕሬዝዳንቱ ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ አቶ ባጢሶ ዌድሶ መድረኩን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር ፥ በክልሉ በሁሉም ዘርፎች በፓርቲ መሪነት የመንግስትና የድርጅት ስራዎች የተሻለ ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም ፤ ለቀጣይ ይህን ውጤት በዘላቂነት ለመቀጠል ሌብነትንና ብልሹ አሰራሮች ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለውጥ ለማምጣት ብርቱ ትግል በማድረግ የቤተሰብ ብልጽግናን በማረጋገጥ አመራሩና አባሉ በቁርጠኝነት መምራትና ለውጤት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የጤና ቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው በቢሮአችን ”ለላቀ ውጤት እንስራ ” በሚል የተጀመረው ክልላዊ ኢንሼቲቪ የመጣው ውጤት አበረታች ቢሆንም አሁንም በየደረጃው በሚገኙ ጤና ተቋማት የአገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ ተጨማሪ ሥራ የሚጠይቁ ጉዳዮች መኖራቸውንና የቀጣይ ትኩረት አጀንዳ እንደሆነም ገልጸዋል።
በመድረኩ የ2016 አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ የሚያሳይ ሰነድ እየቀረበ ሲሆን ፤ በመጨረሻ ሰፊ ውይይትም የሚደረግ ይሆናል።
በመድረኩ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንት ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ፣ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ፣ የቢሮው ማኔጅመንት ፣ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች እና እንዲሁም አባላትና ደጋፊ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
የሲዳማ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ
ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም
- by admin
- on September 30, 2024
0