Sidama Hawassa
+251-462-12-6495
dagoomuf@sidaamaphi.org

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል (South West Ethiopia) ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል በአቶ ታምራት ቦጋሌ የሚመራ ቡድን ከሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የልምድ ልውውጥ አድርጓል።

የሲዳማ ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ለመጡ ልዑካን ቡድን አባላትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት ካስተላለፉ በኃላ በአጠቃላይ በኢንስቲትዩቱ ደረጃ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በመቀጠልም እንግዶቹ በተቋሙ ከሚገኙ ዳይሬክተሮች አማካኝነት የሥራ ምልከታና ልምድ ልውውጥ አድርገዋል። በተጨማሪም የልዑካን ቡድን አባላት በርካታ ምርጥ ሥራዎች እንደተሰሩ በአስተያየታቸው ገልጸዋል።

በክልላችን እደዚህ አይነት ልምድ ልውውጥ ሲካሄድ የዛሬው 7ኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ በፊት ከሞዛምቢክ ሀገር፤ የጋምቤላ፣ የአፋር ክልል ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣አድስ አበባ እና የትግራይ እና ኦሮምያ ክልል ጤና ቢሮ የልምድ ልውውጥ ማካሄዳቸው ይታወሳል። ይህ የሚያሳው ኢንስቲትዩታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ እና አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ መምጣቱን ያሳያል።

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት
ሲዳማ/ሀዋሳ
19/05/2017 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *