በሲዳማ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በዛሬው ዕለት ከመጋቢት 18-21/2018 ዓ. ም ድረስ ለሚካሄደው 5ኛ ዙር የተቀናጀ የልጅነት ልምሻ /ፖሊዮ/ በሺታን መከላከያ ክትባት ዘመቻን አስመልክቶ ለክልሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ለአጋር ድርጅቶች በድጋፋዊ ጉብኝት /Supervision / ላይ ሥልጠና ተሰጥቷል ።

በግንዛቤ ማስጨበጫው መድረክ ላይ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዳመነ ደባልቄ ቤት ለቤት በሚካሄደው ዘመቻ በክልሉ ውስጥ የሚገኝ እያንዳንዱ ዕድሜው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃን ተደራሽ መሆን እንዳለበት ገልጸው ዘመቻው ጥራትን ለማስጠበቅ የተዘጋጀውን የአሠራር መመሪያ ተከትሎ መተግበር እንዳለበት አሳስበዋል።

የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቁጥጥር ዳይረክቶሬት ዳይረክተር አቶ በድሉ ባዴጎ ለክልል ሱፐርቫይዘሮች ዝርዝር የአሠራር መመሪያ እና ስምሪት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል ::

የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

መጋቢት 16/2018ዓ/ም

ሀዋሳ

ተጨማሪ መረጃዎችን የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794

Web site: https://sphi.gov.et/

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *