ጠንካራ የጤና ስርዓትን ለመገንባት የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድን ማጠናከር አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው

__________

የጤና ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሪዞልቭ ቱ ሰቭ ላይቭስ ጋር በመሆን ሲያከናውኑት የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ተቋማት ወረርሽኝን የመከላከል አቅማቸውን ለማሳደግ የተሰራው የሙከራ ስራ ርክክብ ተደረገ።

የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ አሃድን (Primary Care) ማጠናከር በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ካሉ አምስት ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች መካከል ዋነኛው መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገልፀዋል።

የማይበገር የጤና ሥርዓት መገንባት የሚቻለው የጤና ተቋማት ወረርሽኝን የመከላከል፣ የመዘጋጀትና ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅማቸው ጠንካራ ሲሆን መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ደረጄ፤ በተለይም የመጀመሪያ ደረጃ ጤና አሃድ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ ወረርሽኞችን ቀድሞ በመለየትና ሳይዛመቱ በተከሰቱበት አካባቢ ለመቆጣጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው አስገንዝበዋል።

ዶ/ር ደረጄ ክለውም አጋር ድርጅቶችም የመንግሥትን ስትራቴጂ ተከትለው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሳይ ሀይሉ፣ ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት ለወረርሽኝ ዝግጁነትን ከመደበኛ የጤና አገልግሎቶች ጋር ማቀናጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው፣ ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ወቅት መደበኛ አገልግሎቶች ሳይቋረጡ መሰጠታቸው ውጤታማ ስራ መሆኑን ገልጸዋል። በሦስት ክልሎች የተጀመረውን ተሞክሮ በመላ ሀገሪቱ እንዲተገበር ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት በ197 የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የተጀመሩ የሙከራ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገልጿል። እነዚህን መልካም ተሞክሮዎች በአገር አቀፍ ደረጃ በማስፋፋትና ወደ ሙሉ ትግበራ በማሸጋገር፣ የተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር ሥራን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግና ጠንካራና አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመገንባት በትኩረት እንደሚሰራ ተመላክቷል።

በመርሀግብሩ ላይ የሪዞልቭ የኢትዮጵያ ተወካይ እንዲሁም Epdemic Ready Primary Health Care ዳይሬክተርም ተገኝተዋል።

Website: moh.gov.et

Facebook: Ministry of Health,Ethiopia

Twitter: x.com/fmohealth

YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia

Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia

Telegram: t.me/M0H_EThiopia

Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *