የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በቅንጅት መሥራት ለሕብረተሰብ ጤና መረጃዎች ተደራሽነት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ::

በሕብረተሰብ ጤና ዙሪያ የሚሰሩ የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች መካከል የሚፈጠሩ ቅንጅታዊ አሰራሮች ውጤታማ የሕብረተሰብ ጤና ጉዳዮች ላይ መረጃ ለመስጠት እና የሕብረተሰብ ጤና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከተለያዩ በሕብረተሰብ ጤና ዙሪያ ከሚሰሩ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች እንዲሁም ባለሙያዎች ጋር ባካሄደው የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መድረክ ላይ የአንድ ጤና (One Health) ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ፈይሳ ረጋሳ በሰጡት ስልጠና እንደጠቀሱት ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን በብቃት ለመመከትና አስተማማኝ የሕብረተሰብ ጤና ስራዎችን በውጤታማነት ለመፈጸም የጋራ ቅንጅትና የኮሙኒኬሽን ሥራዎች ትኩረት የተሰጣቸው መሆናቸውን ተናግረዋል ።

ዶ/ር ፈይሳ በንግግራቸው፤ በ«አንድ ጤና» (One Health) ትግበራ፣ በዓለም አቀፍ የጤና ደንብ (IHR)፣

በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸውን ተግባራት በማስታወስ፣ የተቋሙን የመቶ ዓመታት ታሪካዊ ጉዞ፣ የወቅቱን የሥራ እንቅስቃሴዎችና አገራዊ ተልዕኮዎችን በተመለከተ ለተሳታፊዎቹ ሰፊ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ታረቀኝ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃውችን በወቅቱ ለሕብረተሰቡ በማድረስ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው በመግለጽ የሕብረተሰብ ጤና ጉዳዮችን፣ የምርምርና የላብራቶሪ ግኝቶችን እንዲሁም የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥርን በተሻለ መንገድ ተደራሽ ለማድረግ በቅንጅት መሥራት ውጤታማ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መረጃዎችን ውጤታማ በሆኑ መረጃ ማሰራጫ ዘመናዊ ዘዴዎች ለሕዝብና ለሚመለከታቸው አካላት ለማድረስ በጋራ የሚሠሩ ሥራዎችን እጅግ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል::

በዚሁ መድረክ ላይ በሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋ ልየታ፣ ቅኝትና ምላሽ አሰጣጥ ሥርዓት እንዲሁም በላብራቶሪ አቅም ግንባታ ዙሪያ ያተኮሩ የሥልጠና ሰነዶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። በቀረቡት መረጃዎችና በተሰጠው ሥልጠና ዙሪያም ተሳታፊዎቹ ከኢንስቲት ሀላፊነቶች አንጻር ሰፊ ምክክር አድርገዋል።

በመድረኩ ማጠናቀቂያ ላይ ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና ጠቃሚ የሥራ ሐሳቦች የተነሱ ሲሆን፣ ለተነሱት ጥያቄዎችም ከኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከተገኙ ኃላፊዎችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ዝርዝር ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ይህ የምክክር መድረክ በኢንስቲትዩቱ እና ከኢንስቲትይቱ ጋር በቅርበት የሚሰሩ የክልል እና የፌዴራል የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች መካከል ያለውን የሥራ ግንኙነት ይበልጥ ለማጎልበት እና ተከታታይነት ያለው ቅንጅታዊ አሠራር ለመተግበር የጋራ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል።

Ministry of Health,Ethiopia

See less

Similar Posts

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *