የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ፣ የሲዳማ ብ/ክ/መ ጤና ቢሮ ማኔጅመንት አባላት፣የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንሰቲትዩት ም/ዋና ዳይረክተር አቶ ኡጋሞ ሀናጋ፣ የEPSS ሀዋሳ ቅርንጫፍ ኃላፊ አቶ ዘመን ለገሰ ፣የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞችን ጨምሮ የዞኖች፣ የወረዳዎችና የጤና ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ የሲዳማ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ዳመነ ዳባልቄ መልዕክት በማስተላለፍ ስብሰባውን በይፋ ከፍተዋል።
የዞን፣ የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያና የወረዳዎች ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ የሆስፒታልና የጤና ጣቢያዎች ሥራ አስኪያጆች፤ አጋር ድርጅቶች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ማኔጅመንት አባላት እና የኢንስቲትዩቱ ጠቅላላ ሠራተኞች በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት በማድረግ ላይ ይገኛሉ ።
የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
ጳጉሜ 4/2018 ዓ/ም
ሀዋሳ
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
![]()
![]()
![]()
ይመልከቱ
ነፃ የስልክ መስመር፡ 7794
Web site: sphi.gov.et/emergency
Facebook: https://web.facebook.com/profile.php?id=100083576610173
Telegram: https://t.me/c/1865772308/1
Email:- admin@sphi.gov.et
See less




























